1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

እነ እስክንድር ነጋ የዋስትና መብት ተከለከሉ

ማክሰኞ፣ መስከረም 19 2013

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ የሕገ መንግሥት እና ጸረ ሽብር ወንጀል ልደታ ምድብ ችሎት አቶ እስክንድር ነጋ እና ሌሎች አራት ተከሳሾችን የዋስትና መብት ውድቅ ሲያደርግ፤ ለአምስተኛ ተከሳሽ  ግን የ30 ሺህ ብር ዋስትና ፈቅዷል።

https://p.dw.com/p/3jAoe
Der Parteiführer von Balderas traf sich mit Bewohnern von Bahrdar
ምስል DW/A. Mekonnen

ለጥቅምት 12 ቀን 2013 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ተይዟል

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ የሕገ መንግሥት እና ጸረ ሽብር ወንጀል ልደታ ምድብ ችሎት አቶ እስክንድር ነጋ እና ሌሎች አራት ተከሳሾችን የዋስትና መብት ውድቅ ሲያደርግ፤ ለአምስተኛ ተከሳሽ  ግን የ30 ሺህ ብር ዋስትና ፈቅዷል። ችሎቶ የእነ እስክንድር ነጋ ጠበቆችን የክስ መቃወሚያ እና የአቃቤ ሕግን ምላሽ አዳምጦ ብይን ለመስጠት ለጥቅምት 12 ቀን 2013 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል። 

ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር
ማንተጋፍቶትስ ስለሺ
ኂሩት መለሰ