እስክንድር ነጋ ተሸለመ
ሐሙስ፣ ሚያዝያ 19 2009ማስታወቂያ
ዓለም ዓቀፉ የፕሬስ ተቋም በምህፃሩ አይፒአይ በእሥር ላይ የሚገኘውን ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን የ9 ኛው የዓለም የፕሬስ ነፃነት ጀግና ሲል ሰየመ። መቀመጫውን ኦስትሪያ ቭየና ያደረገው ተቋም ይህን መሰሉን ሽልማት የሚሰጠው ራሳቸውን ለአደጋ በማጋለጥ ለፕሬስ ነጻነት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላደረጉ ጋዜጠኞች ነው። በኢትዮጵያ መንግሥት በአሸባሪነት የ18 ዓመታት እሥራት የተፈረደበት እስክንድር ከዛሬ 5 ዓመት ከ7 ወር ወዲህ በእርስ ላይ ይገኛል። ስለ እስክንድር ሽልማት ዶቼቬለ ያነጋገራት ባለቤቱ ሰርካለም ፋሲል ሽልማቱ የርሱ ብቻ ሳይሆን በእስር ላይ ለሚገኙ እና ለተሰደዱ ጋዜጠኞች ጭምር ነው ብላለች።
መክብብ ሸዋ
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ