ውዝግቦችአፍሪቃ
እስራኤል እና ሊባኖስ የተኩስ አቁም ስምምነቱን ለሦስት ሳምንት ማራዘማቸው
ዓርብ፣ ሚያዝያ 16 2018
ማስታወቂያ
እስራኤል እና ሊባኖስ የተኩስ አቁም ስምምነቱን በሦስት ሳምንታት ለማራዘም ተስማምተዋል ሲሉ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አሳውቀዋል። ስምምነቱ የመጣው የእስራኤል እና የሊባኖስ ባለሥልጣናት ዋይት ሀውስ ውስጥ ያልተለመደ ስብሰባ ካደረጉ በኋላ እንደሆነ ተገልጿል። በሌላ በኩል በመካከለኛው ም|ሥራቅ የቀጠለውን ውዝግብና ውጥረት ለማርገብ ፓኪስታን የጀመረቸው የሰላም ድርድርን ቀጥላበታለች። በዛሬው ዕለትም የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ወደ ፓኪስታን መጓዛቸው ተሰምቷል።
የመካከለኛው ምሥራቅ ውዝግብ ባያባራም የተኩስ አቁም ስምምነቶች ስለመራዘማቸውና የዓለም ኤኮኖሚ ባናጋው የሆርሙዝ ሰርጥ አካባቢ ስለቀጠለው ውጥረት የዋሽንግተን ዲሲ ዘጋቢያችን አበበ ፈለቀን ወደ ስቱዲዮ ከመግባታችን አስቀድሞ በስልክ አነጋግሬዋለሁ።
አበበ ፈለቀ
ሸዋዬ ለገሠ
ማንተጋፍቶት ስለሺ