1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

እርቀ ሰላምና መረጋጋት ለፍትሀዊና ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ

ረቡዕ፣ ጥር 19 2013

በውይይት መድረኩ በሀገሪቱ የመጣውን ለውጥ ተከትሎ በተለያዩ አካባቢዎች እየተፈጠረ ላለው የሰላም ችግር መፈታት የሚያግዝ የሶማሌ ክልል ጥረትን በተመክሮነት የሚያሳይ መረጃ ቀርቧል። የሰላም ሚንስትር የፖሊሲ ጉዳይ አማካሪ ዶ/ር ሳሙኤል ተፈራ ውይይቱን የሶማሌ ክልል አንፃራዊ ሰላም ተመክሮን ለሌሎች ማካፈል የተቻለበት መድረክ ነው ብለዋል፡፡

https://p.dw.com/p/3oUgg
Äthiopien Jigjiga | Friedenskonferenz
ምስል Mesay Tekelu/DW

እርቀ ሰላም እና መረጋጋት ለፍትሀዊና ዲሞክራሲያዊ  ስርዓት ግንባታ

«የድህረ ለውጥ ተግዳሮቶችና ስኬቶች በሶማሌ ክልል» የሚል መሪ ሀሳብ ያለው የውይይት መድረክ ሰሞኑን በጅግጅጋ ከተማ ተካሂዷል። በሰላም ሚንስቴር እና በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ትብብር በተዘጋጀው መድረክ አራት ያህል ጥናታዊ ፅሁፎች ቀርበው ውይይት ተካሂዶበታል።የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር በሽር አብዱላሂ ለዶይቸ ቬለ (DW) በስልክ በሰጡት መረጃ እንደገለፁት በውይይት መድረኩ በሀገሪቱ የመጣውን ለውጥ ተከትሎ በተለያዩ አካባቢዎች እየተፈጠረ ላለው የሰላም ችግር መፈታት የሚያግዝ የሶማሌ ክልል ጥረትን በተመክሮነት የሚያሳይ መረጃ ቀርቧል።በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ማህበራዊ ሳይንስ ኮሌጅ የአፍሪካ እና እስያ ጥናት እና ምርምር ማዕከል ረዳት ፕሮፌሰር እና የሰላም ሚንስትር የፖሊሲ ጉዳይ አማካሪ ዶ/ር ሳሙኤል ተፈራ በበኩላቸው ውይይቱን በሶማሌ ክልል የመጣውን አንፃራዊ ሰላም ተመክሮ ለሌሎች ማካፈል የተቻለበት ጥሩ መድረክ ነው ብለዋል፡፡ቀደም ሲል በሀገሪቱ ባህልና ቱሪዝም ዘርፍ ሲሰራ የነበረ ስራ ትልቁን ሀገራዊ ስዕል ወደ ጎን የተወ ነው በሚል ሲወቀስ እንደነበር ያነሱት ዶ/ር ሳሙኤል እነዚህን ችግሮች ከመሰረቱ ለመቅረፍ መሰራት በታዳጊዎች ላይ መሰራት እንዳለበት ጠቅሰው ከዚህ በተጨማሪ በተለያየ የጊዜ ምዕራፍ ከህፃናት ውጭ ባለው ማህበረሰብ ላይ መስራት ይገባል ብለዋል።የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር በሽር የተገኘውን ሰላም በመጠቀም  ስራ አጥነትን ለመቅረፍ እንደሚሰሩ ተናግረዋል።
መሳይ ተክሉ

Äthiopien Jigjiga | Friedenskonferenz
ምስል Mesay Tekelu/DW

ኂሩት መለሰ 

አዜብ ታደሰ