1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

እልባት ያላገኘው የኦነግ አመራሮች ውዝግብ

ዓርብ፣ ጥር 21 2013

በወርሃ ሃምሌ 2012 ዓ.ም. በኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) አመራሮች መሃከል የተፈጠረው አለመግባባት ቡድኖቹ ለብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ባስገቡት አቤቱታ መሰረት ቦርዱ ታህሳስ 09 ቀን 2013 ዓ.ም. የሰጠው እልባት ተግባራዊ አለመሆኑ ቅሬታ አስነሳ፡፡

https://p.dw.com/p/3oaH3
 Logo Oromo Liberation Front

እልባት ያላገኘው የኦነግ አመራሮች ውዝግብ

በወርሃ ሃምሌ 2012 ዓ.ም. በኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) አመራሮች መሃከል የተፈጠረው አለመግባባት ቡድኖቹ ለብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ባስገቡት አቤቱታ መሰረት ቦርዱ ታህሳስ 09 ቀን 2013 ዓ.ም. የሰጠው እልባት ተግባራዊ አለመሆኑ ቅሬታ አስነሳ፡፡
የኦሮሞ ነጻነት ግንባር የህዝብ ግንኙነት ኃላፊና ከፓርቲው ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ ጋር ውዝግብ ውስጥ ከገቡት አቶ ቀጄላ መርዳሳ እንደሚሉት የቦርዱ ውሳኔ በአቶ ዳውድ ኢብሳ በኩል ተቀባይነት በመነፈጉ ዳግም ለቦርዱ አቤት ለማለት ተገደናል ይላሉ፡፡
በአቶ ዳውድ ኢብሳ በኩል ግዜያዊ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ሆነው እያገለገሉ ያሉት አቶ በቴ ዑርጌሳ እንደሚሉት ግን በኦሮሞ ነጻነት ግንባር አመራሮች መሃል ተፈጠረ ቁርሾ የለም፡፡ ፓርቲውን አሁን እያሳሰበው ያለውም የአመራሮቹ እስራት እና አዲስ አበባ ያለው ዋና ቢሮውም ጭምር በፖሊስ መዘጋት ነው ብለዋል፡፡
የአዲስ አበባ ፖሊስ በበኩሉ ሰላምን የማስጠበቅ እንጂ ወደ ቢሮው እንዳይገባ የተከለከለ የኦነግ አመራር እንደሌለና ቢሮውም ክፍት መሆኑን ነው የሚገልፀው፡፡
ስዩም ጌቱ 
አዜብ ታደሰ