1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኤድዋርዶ ሞንድሌን

Carla Fernandes
ሐሙስ፣ መጋቢት 24 2012

ኤድዋርዶ ሞንድሌን ፍሬሊሞ የተሰኘው የሞዛምቢክ ነጻ አውጪ ንቅናቄ መሪ ሆነው አገልግለዋል። የሠላ አዕምሮ ከነበሯቸው አፍሪቃውያን አንዱ የሆኑት ሞንድሌን ምንም እንኳን የታገሉለት ነፃነት እውን ሲሆን ለማየት ባይበቁም የሞዛምቢክ መስራች አባት ተብለው ይጠራሉ።

https://p.dw.com/p/3ZD2I
African Roots  | Eduardo Mondlane

ኤድዋርዶ ሞንድሌን መቼ እና የት ተወለዱ? 
ኤድዋርዶ ቺቫምቦ ሞንድሌን እ.ጎ.አ. ሰኔ 20፤ ቀን 1920 ዓ.ም ደቡብ ሞዛምቢክ በምትገኘው የጋዛ አውራጃ ማንጃካዜ ከተማ ተወለዱ። 10 ዓመት እስኪሞላቸው ድረስም እረኛ ነበሩ።  

ኤድዋርዶ ሞንድሌን በየትኛው ትምህርት ነበር የታነፁት? 
ሞንድሌን ማንጃካዜ በአቅራቢያቸው በሚገኝ የስዊዘርላንድ የሚሲዮን ትምህርት ቤት ነው የተማሩት። ኋላም አንትሮፖሎጂ እና የማኅበረሰባዊ ሳይንስ በደቡብ አፍሪቃ (ለአጭር ጊዜ) እና ፖርቹጋል ውስጥ አጥንተዋል። እዛም ነው የጊኒ ቢሳው አሚልካር ካብራል፣ የካፕ ቬርዴ እና የአንጎላው አጎስቲንሆ ኔቶን የመሳሰሉ የአፍሪቃ ፀረ ቅኝ ግዛት ታጋዮችን የተዋወቁት።  
ከዛም ትምህርታቸውን ለማጠናቀቅ እና የዶክትሬት ዲግሪያቸውን ለመያዝ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ሄዱ። እዛ በነበራቸው ቆይታም በሲራኩስ ዩንቨርስቲ ያስተምሩ ነበር። ኋላም የተባበሩት መንግስታት ባለአደራ ምክር ቤት ውስጥ የአፍሪቃ ሃገራትን ከቅኝ ግዛት ማላቀቅ ጋር የተያያዙ ጥናቶች እንዲያከናውኑ ተመራማሪ ሆነው ተቀጠሩ።  ከዚያም ባሻገር በካሜሮን እና በናይጄሪያ መካከል ያለውን የድንበር ወሰን የሚለየውን የብሪታንያ - ካሜሮን ህዝበ ውሳኔ አብረው አዘጋጅተዋል። 

ኤድዋርዶ ሞንድሌን የታወቁት በምንድን ነው?
ታንዛኒያ ዳሬ ሰላም ውስጥ እ.ጎ.አ. የመጀመሪያው የፍሬሊሞ (FRELIMO) የሞዛምቢክ ነፃ አውጭ ግንባር ፕሬዚዳንት እና ተባባሪ መስራች ነበሩ። ግንባሩም ከሞንድሌን ሞት በኋላ የሞዛምቢክን ነፃነት ሊያስከብር ችሏል። ሞንድሌን አብዮተኛ፣ የአፍሪቃ አንድነት አቀንቃኝ፣ ዓለም አቀፋዊ እና አንትሮፖሎጂስት ናቸው።  

African Roots  | Eduardo Mondlane
ሞንድሌን 10 ዓመት እስኪሞላቸው ድረስም እረኛ ነበሩ።

ኤድዋርዶ ሞንድሌን

ኤድዋርዶ ሞንድሌን እንዴት ይመሠገናሉ? 
ሞንድሌን በብዙኃን ዘንድ ሞዛምቢክን አንድ ለማድረግ በነበራቸው ራእያቸው አኹንም ድረስ ይመሠገናሉ።  እሳቸውም ግሩም በሆኑ የትምህርት ማስረጃዎች የተደገፉ ነበሩ።
ኤድዋርዶ ሞንድሌን እንዴት ሞቱ? 

ሞንድሌን እ.ጎ.አ. የካቲት 3 ቀን፤ 1969 ዳሬ ሰላም ውስጥ አንድ ቦምብ የተጠመደበት ጥቅል ሲከፍቱ ነው ሕይወታቸው ያለፈው፡፡ ከአደጋው በስተጀርባ የነፃ አውጪው ንቅናቄ የፖለቲካ ተቀናቃኛቸው አልያም የፖርቹጋል የስለላ ድርጅት ነው ያለው ቢባልም ምክንያቱ ግን እንቆቅልሽ እንደኾነ ቀርቷል። 
ኤድዋርዶ ሞንድሌን መጽሐፍ ጽፈው ነበር ይሆን?

ኤድዋርዶ ሞንድሌን በርካታ መጽሐፍትን ጽፈዋል። ከነዚህም መካከል 'Lutar por Moçambique' (ትግል ለሞዛምቢክ) የሚለው እና ከኅልፈታቸው ብዙም ሳይቆይ የታተመው መጽሐፋቸው ይገኛል። ይህም የብሔራዊ ንቅናቄው እንቅስቃሴ በርካታ ሠነዶችን ያካተተ እንደሆነ ይነገራል።   

የሞዛምቢክ መንግሥት ኤድዋርዶ ሞንድሌን ምን አይነት ክብር ለገሳቸው? 

ቀደም ሲል በፖርቹጋል ሥርዓት ስር የሎሬንሶ ማርከስ የሚባለው እና ሞዛምቢክ መዲና ማፑቶ የሚገኘው ዩኒቨርሲቲ ከቅኝ ግዛቱ ነፃነት በኋላ 1975 ኤድዋርዶ ሞንድሌን በሚለው ስማቸው ተተክቷል።   

ኤድዋርዶ ሞንድሌን


ይህ ዘገባ አፍሪቃዊ ሥረ-መሠረት በሚል ከጌርዳ ሔንክል ተቋም ጋር በመተባበር የሚቀርብ ዝግጅት ነው። የዘገባው ሳይንሳዊ ምክር የተገኘው ከፕሮፌሰር ጉዳዬ ኮናቴ፣ ሊሊ ማፌላ Ph.D እና ፕሩፌሰር ክሪስቶፈር ኦግቦግቦ ነው።