1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢጣሊያ እና የአዉሮጳ ሕብረት ጉዞ

ዓርብ፣ ግንቦት 24 2010

አምስት ኮኮብ እና ሊጋ የተባሉት የፖለቲካ ፓርቲዎች ከዚሕ ቀደም ያቀረቡትን ካቢኔ የኢጣሊያ ፕሬዝደንት ሰርጂዎ ማታሬላ ዉድቅ አድርገዉት ነበር።ከብዙ ዉዝግብ፤ድርድር እና ሽምግልና በኋላ ዛሬ የተመሠረተዉ መንግሥት የካቢኔ አባላት ከቦታ ለዉጥ በስተቀር ካለፈዉ ብዙም የተለዩ አይደሉም

https://p.dw.com/p/2yoUL
Italien, Rom: Ankunft Giuseppe Conte am Montecitorio Palast
ምስል picture-alliance /A. Lingria

(Q&A) Italien neue Regierung - MP3-Stereo

ኢጣሊያ ዉስጥ ባለፈዉ መጋቢት በተደረገዉ ምርጫ ከፍተኛ ድምፅ ያገኙት ቀኝ አክራሪ «ሕዝበኛ» ፓርቲዎች ዛሬ ተጣማሪ መንግስት መሰረቱ። አምስት ኮኮብ እና ሊጋ የተባሉት የፖለቲካ ፓርቲዎች ከዚሕ ቀደም ያቀረቡትን ካቢኔ የኢጣሊያ ፕሬዝደንት ሰርጂዎ ማታሬላ ዉድቅ አድርገዉት ነበር።ከብዙ ዉዝግብ፤ድርድር እና ሽምግልና በኋላ ዛሬ የተመሠረተዉ መንግሥት የካቢኔ አባላት ከቦታ ለዉጥ በስተቀር ካለፈዉ ብዙም የተለዩ አይደሉም።የአዉሮጳ ሕብረትን መርሕ እና ስደተኞችን የሚጠሉት  ፖለቲከኞች ሥልጣን መያዛቸዉ የአዉሮጳ ሕብረት አባል ሐገራት ፖለቲከኞችን እያነጋገረ ነዉ።የሮም ወኪላችን ተኽለ እግዚ ገብረየሱስን በስልክ አነጋግሬዉ ነበር።

ተኽለ እግዚ ገብረየሱስን

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ