ኢዴፓ እና የምርጫ ቦርድ ውሳኔ
ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 14 2012ማስታወቂያ
ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሕጋዊ እውቅና ማግኘቱን ያሳወቀው የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ኢዴፓ ምርጫው የሚካሄድ ከሆነ እንደሚሳተፍ አስታወቀ።በፓርቲው እምነት ግን ምርጫ መካሄድ የለበትም።የኢዴፓ ብሔራዊ ምክር ቤት አባል አቶ ልደቱ አያሌው ለዶቼቬለ በሰጡት ቃለ ምልልስ ፓርቲያቸው ፣አሁን ኢትዮጵያ የምትገኝበት ሁኔታ ነጻ ፍትሃዊ እና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ማካሄድ የሚያስችል ነው ብሎ አያምንም።አቶ ልደቱ ከዚሁ ጋር ፓርቲውን ለዓመታት ሲያወዛግብ የቆየው ጉዳይ እልባት ማግኘቱንም ተናግረዋል።ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ዝርዝሩን አዘጋጅቷል።
ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ