1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢዜማ እጩ ተወዳዳሪዎቹን መለየት ጀመረ 

ሰኞ፣ ጥር 17 2013

የፖለቲካ ተሣትፎን፣ የሥራ ልምድንና ሕዝባዊ አገልግሎትን ተወዳዳሪ ሆኖ ለመቅረብ በመስፈርትነት ማስቀመጡን የሚናገረው፣ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ መምጣት በኋላ የተመሰረተው ኢዜማ  እጩ ተወዳዳሪዎቹን ከያዝነው ጥር አንስቶ በግልፅ ውድድር መለየት መጀመሩን ገልጿል።

https://p.dw.com/p/3oOYO
Äthiopien Berhanu Nega
ምስል Privat

ኢዜማ እጩ ተወዳዳሪዎቹን መለየት ጀመረ 

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) በስድስተኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ ለሕዝብ ተወካዮች እና የአዲስ አበባ ምክር ቤት ፓርቲውን ወክለው የሚወዳደሩ አባላቱን እርስ በርስ እያወዳደረ መለየት መጀመሩን ይፋ አድርጓል።  የፖለቲካ ተሣትፎን፣ የሥራ ልምድንና ሕዝባዊ አገልግሎትን ተወዳዳሪ ሆኖ ለመቅረብ በመስፈርትነት ማስቀመጡን የሚገልፀው፣ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ መምጣት በኋላ የተመሰረተው ኢዜማ  እጩ ተወዳዳሪዎቹን ከያዝነው ጥር አንስቶ በግልፅ ውድድር መለየት መጀመሩን ገልጿል። በፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የሚመራው ኢዜማ ቀጣዩ ምርጫ ነፃ፣ ፍትሓዊ እና ተቀባይነት ያለው እንዲሆን ፅኑ ፍላጎቱ መሆኑን በተለያዩ ጊዜያት ባወጣቸው መግለጫዎቹ ተናግሯል ። 
ሰሎሞን ሙጬ 
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ