ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በሳዑዲ ማጎሪያዎች
ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 7 2013ማስታወቂያ
ሳዑዲ አረብያ የኢትዮጵያውያን ስደተኞችን አያያዝ እንድታሻሻል ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ሂዩመን ራይትስ ዋች ቢጠይቅም ቀና ምላሽ እንዳላገኘ አስታወቀ። በድርጅቱ የፍልሰተኞችና ስደተኞች መብት ክፍል ሃላፊ ቢል ፍሬሊክ ለዶቼቬለ እንደተናገሩት ኢትዮጵያውያኑ ስደተኞች ሳዑዲ በሚገኙ የስደተኞች ማጎሪያ ማዕከላት በኢሰብዓዊ መንገድ ነው የተያዙት።አሁን ያሉበት ሁኔታም አስደንጋጭና አሳዛኝ ነው። ድርጅቱ በሃገሪቱ የስደተኞች ማጎሪያ ማዕከላት የሚገኙ ኢትዮጵያንን አነጋግሮ ትናንት ይፋ ባደረገው ዘገባው እንደገለጸው በኢሰብዓዊው አያያዝ ምክንያት ከጥቅምት ወዲህ ቢያንስ የሦስት ሰዎች ሕይወት አልፏል።ከአትላንታ ዩናይትድ ስቴትስ ታሪኩ ኃይሉ ተጨማሪ ዘገባ አሰናድቷል።
ታሪኩ ኃይሉ
ኂሩት መለሰ
እሸቴ በቀለ