1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢትዮጵያዊነት የዜጎች ማስከበሪያ ጉባኤ በኢትዮጵያ ኢንስቲትዩት ሊከፍት ነው

ቅዳሜ፣ ነሐሴ 11 2011

በአሜሪካ ከአምስት ዓመት በፊት የተቋቋመው ኢትዮጵያዊነት የዜጎች ማስከበሪያ ጉባኤ የተሰኘው ድርጅት በኢትዮጵያ ኢንስቲትዩት ለመክፈት እየተዘጋጀ እንዳለ አስታውቋል። ኢንስቲትዩቱ በኢትዮጵያውያን የጋራ ታሪክ፣ የጋራ እሴቶች፣ ባህል እና አንድነት ላይ አተኩሮ የመስራት እቅድ አለው ተብሏል።

https://p.dw.com/p/3O4K7
Äthiopien Adwa Feier in Addis Abeba
ምስል DW/S. Muchie

ኢንስቲትዩቱ የጋራ ታሪክ እና እሴቶች ላይ ያተኩራል ተብሏል

ኢትዮጵያዊነት የዜጎች ማስከበሪያ ጉባኤ በዩናይትድ ስቴትስ፣ አውሮፓ እና ሌሎች አካባቢዎች ደጋፊ እና አባላት እንዳሉት በአሜሪካ ቺካጎ ክፍለሀገር የሚኖሩት የድርጅቱ ሊቀመንበር ዶ/ር እርቁ ይመር ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅት ደግሞ ድርጅቱ ኢትዮጵያ ውስጥ ገብቶ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ነው ብለዋል። 

ድርጅቱ ከዚህ ቀደም በተለያዩ ጊዜያት በህገ መንግስት፣ በምጣኔ ሀብት፣ በትምህርት እና በሌሎችም ጉዳዮች ጥናታዊ ጽሁፎችን ማቅረቡን ሊቀመንበሩ ያስረዳሉ። ከእነዚህ ጥናታዊ ጽሁፎች ውስጥ ሶስቱ ታትመው በታላላቅ የትምህርት ተቋማት እንደሚገኙም ገልጸዋል። አሁን ድርጅታቸው በኢትዮጵያዊነት የጋራ እሴት ላይ ያተኮረው ላለፉት 30 ዓመታት ኢትዮጵያዊነት በመደብዘዙ ነው ብለዋል። 
 

ሙሉ ጥንቅሩን ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ።  

መክብብ ሸዋ 

ተስፋለም ወልደየስ