1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

 ኢትዮጵያ ጦርነት፣አሜሪካና የምሁራን አስተያየት

ሐሙስ፣ ኅዳር 9 2014

የአትላንታዉ ወኪላችን ታሪኩ ኃይሉ ያነጋገራቸዉ በኒዮርክ ዩኒቨርሲቲ የታሪክና የፖለቲካ መምህር ፕሮፌሰር ገላውዴዎስ አርአያ አሜሪካ ጦርነቱ ቆሞ ውይይት እንዲጀመር የምታደርገውን ጫና  «የሚደግፍ» ብለዉታል።

https://p.dw.com/p/43C6f
Weltspiegel 09.02.2021 | USA Impeachment | Washington Capitol Hill
ምስል Sarah Silbiger/Getty Images

የኢትዮጵያ ጦርነት፣ የዩናይትድ ስቴትስ አቋምና ምሁራን

ኢትዮጵያ መንግሥትና ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ከየደጋፊዎቻቸዉ ጋር ሆነዉ የገጠሙትን ጦርነት ለማስወገድ ዩናይትድ ስቴትስ የምታደርገዉ ጥረትና ጫና እዚያዉ ዩናይትድ ስቴትስ ከሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን አሜሪካዉያን ምሑራን ዘንድ ድጋፍም ተቃዉሞም ገጥሞታል። የአትላንታዉ ወኪላችን ታሪኩ ኃይሉ ያነጋገራቸዉ በኒዮርክ ዩኒቨርሲቲ የታሪክና የፖለቲካ መምህር ፕሮፌሰር ገላውዴዎስ አርአያ አሜሪካ ጦርነቱ ቆሞ ውይይት እንዲጀመር የምታደርገውን ጫና  «የሚደግፍ» ብለዉታል። የኢትዮጵያና ኤርትራን ግንኙነት በቅርብ የሚከታተሉት ዶክተር በርኼ ሀብተጊዮርጊስ ግን የአሜሪካ ሚና ሰላም አያመጣም ባይ ናቸው።

ታሪኩ ኃይሉ

ነጋሽ መሐመድ

ኂሩት መለሰ