1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢትዮጵያ ዶላር መር ዓለም አቀፍ የቦንድ ሽያጯ ጨመረ

ረቡዕ፣ ሐምሌ 11 2010

ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሃገራት ጋር በጀመረችው የሰላም ሥምምነት እንዲሁም በምጣኔ ሃብት እና በፖለቲካ ማሻሻያ እርምጃዎቿ ምክንያት ባለፉት ቀናት ዶላር መር የሆነው ዓለም አቀፍ የቦንድ ሽያጯ በእጅጉ ጨምሮ መታየቱ ተሰምቷል።

https://p.dw.com/p/31haa
Äthiopien Währung Birr
ምስል DW/Eshete Bekele Tekle

ለጭማሪው በኢትዮጵያ የታየው የለውጥ ተስፋ አንዱ ምክንያት ነው

በስታንዳርድ ባንክ ቡድን የአፍሪቃ ጥናት ተመራማሪ እና የምሥራቅ አፍሪቃ ከፍተኛ የምጣኔ ሃብት ባለሞያ ሚስተር ጂብራን ቁረይሽ በተለይ ለዶይቸ ቬለ በሰጡት ማብራሪያ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ በኢትዮጵያም ሆነ በምሥሪቅ አፍሪቃ ቀጠና እያደረጉ ያሉት በጎ የለውጥ ጅማሮ የገበያ ሥርዓትቱን ከማጠናከሩም በላይ ባለሃብቶች ለኢትዮጵያ ቦንድ የተሻለ ፍላጎት እና መተማመን አሳድሮባቸዋል ብለዋል። ዝርዝሩን እንዳልካቸው ፈቃደ አጠናቅሮታል ።

እንዳልካቸው ፈቃደ

ሸዋዬ ለገሠ

አዜብ ታደሰ