1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢትዮጵያ ያልተለመደዉ ጉምና ጭጋግ

ሐሙስ፣ ሐምሌ 22 2013

አዲስ አበባን ጨምሮ ደጋማዉን የኢትዮጵያ አካባቢ የጋረደዉ ጉምና ደመና የየአካባቢዉ ነዋሪን የዕለት ከዕለት እንቅስቃሴን እያጎለ ነዉ።

https://p.dw.com/p/3yHeY
Äthiopien Addis Ababa | Winter
ምስል Seyoum Getu/DW

ያልተለመደዉ ጉምና ጭጋግ

አዉሮጳና እስያን ያስጨነቀዉ ጎርፍና የዝንባ አደጋ ኢትዮጵያም መድረሱ እንደማይቀር የሚትሪዮሎጂ ባለሙያዎች እያስጠነቀቁ ነዉ። አዲስ አበባን ጨምሮ ደጋማዉን የኢትዮጵያ አካባቢ የጋረደዉ ጉምና ደመና የየአካባቢዉ ነዋሪን የዕለት ከዕለት እንቅስቃሴን እያጎለ ነዉ። የአዲስ አበባ ነዋሪዎች እንደሚሉት ዘንድሮ ያጋጠማቸዉ የጉም ግርዶሽና  ቅዝቃዜ ከዚሕ ቀደም አይተዉት የማያዉቁት ዓይነት ነዉ። የኢትዮጵያ የሚትሪዮሎጂ ባለሙያዎች እንደሚሉት እይታን የሚጋርደዉ ጉም የበረራን እንቅስቃሴን ሊያዉክ ይችላል። በየአካባቢዉ የሚጥለዉና ይጥላል ተብሎ የሚጠበቀዉ ከባድ ዝናብ  ደግሞ በርካታ አካባቢዎችን ሊያጥለቀልቅ እንደሚችል ባለሙያዎቹ እያስጠነቀቁ ነዉ።

Äthiopien Addis Ababa | Winter
ምስል Seyoum Getu/DW

ስዩም ጌቱ 

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሠ