ኢትዮጵያ በዓለም አቀፉ የቅርስ ጥበቃ ተቋም የኮሚቴ አባል ሆና ተመረጠች
ዓርብ፣ ኅዳር 19 2012ማስታወቂያ
ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግስታት የትምህርት የሳይንስ እና ባህል ተቋም ዩኔስኮ የአለም ቅርስ ጥበቃ ኮሚቴ አባል ሀገር ሆና ተመርጣለች። ኢትዮጵያ በአለም አቀፉ የቅርስ ጥበቃ ተቋም የኮሚቴ አባል ሆና በመመረጧ ለዓለም ቅርሶች ጥበቃ ትኩረት እንዲሰጥ የበኩሏን አስተዋጽዖ እንድታበረክት ዕድል ይፈጥርላታል ተብሏል። ኢትዮጵያ በአባልነት የተመረጠችው ሰሞኑን ፓሪስ ላይ በተካሄደው የዩኔስኮ የቅርስ ጥበቃ ኮንቬሽን አባል አገራት ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ነው።
ሃማኖት ጥሩነህ
ታምራት ዲንሳ
ተስፋለም ወልደየስ