ኢትዮጵያ በውጭ የሚገኙ ዜጎች በባንክ ሥራ እንዲሰማሩ የመፍቀዷ ፋይዳ
ማክሰኞ፣ ሐምሌ 30 2011ማስታወቂያ
በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የተሻሻለው የባንክ አሰራር ህግ የውጭ ምንዛሪ ግኝትንና ከውጭ የሚገኝ የፋይናንስ ሃብትን የሚያሳድግ ውሳኔውም ተገቢ ግን የዘገየ መሆኑን የዘርፉ ባለሙያ ተናገሩ።
የህግ ማሻሻያ ጥያቄው በሁሉም የአለም አቅጣጫ ካሉ ዳያስፖራ ኢትዮጵያዊያን በየጊዜው ሲነሳ የነበር መሆኑም በሃገሪቱ የባንክ ልማት ዘርፍ ጉልህ በጎ ተጽእኖ የሚኖረው ነው ተብሏል።
ነባሩ ህግ ኢትዮጵያዊያንን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያንን ከዚህ ስራ አርቆ የቆየ በመሆኑ የፋይናንስ ሴክተሩ ተወዳዳሪና ጠንካራ እንዳይሆን አድርጎት መቆየቱን በኮተቤ ሜትሮ ፖሊታን ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑት ዶክተር መኮንን ካሳሁን ተናግረዋል።
ዳያስፖራው እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ ሸር የመግዛት ፣ ባለቤት የመሆንና ባንክ የመቋቋም መብቱ በህግ መፈቀዱ የረጅም ጊዜ የመብት ጥያቄው መመለሱን ያረጋገጠበት እና ዝርዝር አሰራሩ ልማት ባንክ በሚያወጣቸው መመርያዎች ይታያል ያሉት የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት ህጉ መሻሻሉን እና እድሉ መከፈቱን ተከትሎ ሊከሰት የሚችልን የጎንዮሽ ጉዳት ለመከላከልም መንግስት ክትትል
ያደርጋል ብለዋል።
ሰለሞን ሙጬ
ኂሩት መለሰ