1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢሠመኮ ጋዜጠኞች እንዲፈቱ ጠየቀ 

ረቡዕ፣ ሐምሌ 7 2013

ኢትዮጵያ ዉስጥ ካለፈዉ ሰኔ ማብቂያ ወዲሕ አዉሎ ሚዲያና ኢትዮ ፎረም ለተባሉ መገናኛ ዘዴዎች የሚዘግቡና የሚሰሩ 12 ጋዜጠኞች መታሠራቸዉን ድንበር የለሽ ዘጋቢዎች የተሰኘዉ ዓለም አቀፍ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት በቅርቡ አስታዉቆ ነበር

https://p.dw.com/p/3wTxy
Äthiopien EHRC  LOGO

የታሰሩ ጋዜጠኞች እንዲለቀቁ ኢሠመኮ ጠየቀ

የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ከፍርድ ቤት ዉሳኔ ዉጪ ያሰሯቸዉን ጋዜጠኞችና የመገናኛ ዘዴ ሠራተኞች ባስቸኳይ እንዲለቅቁ የኢትዮጵያ የሠብአዊ መብቶች ኮሚሽን ጠየቀ።ኢትዮጵያ ዉስጥ ካለፈዉ ሰኔ ማብቂያ ወዲሕ አዉሎ ሚዲያና ኢትዮ ፎረም ለተባሉ መገናኛ ዘዴዎች የሚዘግቡና የሚሰሩ 12 ጋዜጠኞች መታሠራቸዉን ድንበር የለሽ ዘጋቢዎች የተሰኘዉ ዓለም አቀፍ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት በቅርቡ አስታዉቆ ነበር።የኢትዮጵያ መንግስት የሚያስተዳድረዉ የመብት ተሟጋች ድርጅት እንደሚለዉ ጋዜጠኞች በዘፈቀደ መታሠራቸዉ የሐገሪቱን የሕግ ሥርዓት የሚሸረሽር ነዉ።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር 

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሰ