1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢህአዴግ የፖለቲካ ምልከታ ተለውጧል?

ሐሙስ፣ ነሐሴ 3 2010

የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር ኢህአዴግ ጠንካራ ሕዝባዊ ተቃውሞ ከገጠመው በኋላ ራሱን በጥልቅ እንደሚያድስ ገልፆ በርካታ ስብሰባ ግምገማዎችንም አካሂዷል።

https://p.dw.com/p/32uQI
EPRDF Logo

አዲስ የፖለቲካ አካሄድ እየተከተለ ይሆን?

ተቃውሞ በጠናበት ወቅት ስልጣን ላይ የነበሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ስልጣን በፈቃዳቸው ከለቀቁ በኋላ አዲስ ሊቀ መንበር የመረጠው ኢህአዴግ በአሰራሩ መሠረት ሊቀመንበሩን በጠቅላይ ሚኒስትርነት  ከሰየመ ወራት ተቆጠሩ። አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ደግሞ ለዘመናት የሚታወቀውን ኢህአዴግን በአዲስ መልክ ወደኅብረተሰቡ ይዘው ለመቅረብ መሞከራቸው እየታየ ነው። ይህን ርምጃ ኢህአዴግ በአሰራር በአስተሳሰቡ ማለትም በፖለቲካዊ ምልከታው ላይ መሠረታዊ ለውጥ አድርጓል ማለት ያስችል ይሆን? ዳግማዊ ሲሳይ ተድላ የፖለቲካ ተንታኞችን አነጋግሮ ተከታዩን ዘገባ ከብራስልስ ልኮልናል።

ዳግማዊ ሲሳይ ተድላ

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ