1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ሳይንስኢትዮጵያ

ኢ-ቴክ ኢትዮጵያዊ የቴክኒዎሎጂ ኩባንያ

ረቡዕ፣ ጥር 12 2013

21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ከፍተኛ የቴክኖሎጂ አገልግሎት የተዘረጋበት፣ ተፅዕኖውም በየትኛውም ሥፍራ የተለጠጠበት ሆኗል። ቴክኒዎሎጂ የሕይወት መውጣት መውረድን መቀነስ የመቻሉን ያህል ከአጠቃቀም መረዳት ማነስ፣ እንዲሁም ከአቅም ማጠር ጋር በተገናኘ አሉታዊ ውጤት አስከታይ ሲሆን ይስተዋላል።

https://p.dw.com/p/3oC48
Überwachung I Sicherheit und Bedrohungen im Netz
ምስል DW Akademie

ኢ-ቴክ ኢትዮጵያዊ የቴክኒዎሎጂ ኩባንያ

21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ከፍተኛ የቴክኖሎጂ አገልግሎት የተዘረጋበት፣ ተፅዕኖውም በየትኛውም ሥፍራ የተለጠጠበት ሆኗል። ቴክኒዎሎጂ የሕይወት መውጣት መውረድን መቀነስ የመቻሉን ያህል ከአጠቃቀም መረዳት ማነስ፣ እንዲሁም ከአቅም ማጠር ጋር በተገናኘ አሉታዊ ውጤት አስከታይ ሲሆን ይስተዋላል። በእንዲህ ያለው የቴክኖሎጂ ዘርፍ የሰለጠኑ ኢትዮጵያዊያን ወደ ውጭ ሃገራት የማማተርና በሌሎች አገሮች የመሥራት አዝማሚያቸው ከፍተኛ በመሆኑ ለሀገራቸው በሙያቸው የሚያደርጉት እገዛ እዚህ ግባ የሚባል አለመሆኑን በማመን ኢ-ቴክ የተባለ የግል የቴክኖሎጂ ኩባንያ በ200 ሚሊዮን ብር በዚህ አመት ተቋቁሟል። በተለያዩ 11 የቴክኖሎጅ ዘርፎች ላይ እሠራለሁ የሚለው ይህ ተቋም በዋናነት በመተግበሪያ ወይም ሴፍትዌር ማበልፀግ፣ በሳይበር ደኅንነት ፣ በቴሌኮም መሰረተ ልማት እንዲሁም በፋይናንስ ቴክኖሎጅ ዘርፎች ላይ ሥራ ጀምሬያለሁ ብላል።

ሰለሞን ሙጬ

ሸዋዬ ለገሠ