አፍሪቃውያንን ያሳሰበው ደቡብ አፍሪቃ አዲስ ሕግ
ሐሙስ፣ መስከረም 22 2012ማስታወቂያ
ደቡብ አፍሪቃ በአነስተኛ ንግድ ልማት ሚንስትሯ በኩል ልታወጣ ያቀደችው አዲስ ሕግ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ የውጭ ሃገራትን በአንዳንድ አነስተኛ ንግድ ላይ እንዳይሰማሩ የሚያግድ ነው። ይሕ አዲስ ሕግ የውጭ ሃገራት በመጤ ጠል ደቡብ አፍሪቃውያን መጠነ-ሰፊ ጥቃት ከደረሰባቸው በኋላ አንዳቸውም ለደረሳባቸው ጉዳት ካሳ ሳያገኙ የሚወጣ መኾኑ ብዙዎችን አስከፍቷል። የውጭ ሃገራት ጥላቻ የወለደው ሕግ ነው፤ ስለዚህ ተቀባይነት የለውም ሲሉ ደቡብ አፍሪቃ ነዋሪ የኾኑ አፍሪቃውያን ይናገራሉ። ደቡብ አፍሪቃ ነዋሪ ከሆነው ጋዜጠኛ እና የመብት ተሟጋች መላኩ አየለ ጋር ቃለ መጠይቅ አድርገናል።
ማንተጋፍቶት ስለሺ
አዜብ ታደሰ