1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አፍሪቃ በዓለምአቀፉ መድረክ ትልቅ ሚናን ለምን ሻተች?

ቅዳሜ፣ መስከረም 21 2015

የአፍሪቃ መሪዎች በተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እንዲኖር ጥሪ እያቀረቡ ነው። ዶቼ ቬለ ያነጋገራቸዉ አፍሪቃዉያን እንደገለፁት ምዕራባዉያን የአህጉሪቱን ፍላጎት ከልባቸዉ ያጤኑታል የሚል እምነት የላቸዉም። የአፍሪቃ ሕብረት የመንግሥታቱ ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት የተሃድሶ ማሻሻያዎችን እንዲያደርግ ጥሪ ሲያደርግም ቆይቷል።

https://p.dw.com/p/4HbzV
UN-Vollversammlung in New York | Treffen Macron mit Tshisekedi und Kagame
ምስል Ludovic Marin/AFP/Getty Images

የፀጥታ ም/ቤቱን መቀመጫ ለማግኘት ከአፍሪቃ ውጭ ተጨማሪ ድምፆች መጉረፍ አለባቸዉ

በርካታ የአፍሪቃ መሪዎች በተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እንዲኖር ጥሪ እያቀረቡ ነው። ዶቼ ቬለ ያነጋገራቸዉ አፍሪቃዉያን እንደገለፁት ምዕራባዉያን የአህጉሪቱን ፍላጎት ከልባቸዉ ያጤኑታል የሚል እምነት የላቸዉም። የአፍሪቃ ሕብረት የመንግሥታቱ ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት የተሃድሶ ማሻሻያዎችን እንዲያደርግ ጥሪ ሲያደርግም ቆይቷል። ዩናይትድ ስቴትስ፣ ሩስያ፣ ቻይና፣ ፈረንሳይና እና ታላቅዋ ብሪታንያን ያካተተዉና ባለ አምስት ቋሚ አባላትን የያዘዉ የመንግሥታቱ ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ድምፅ አይሆነኝም ሲል የአፍሪቃ ሕብረት ይከራከራል።

USA New York | Macky Sall | Präsident von Senegal und Leiter der Afrikanische Union
ምስል Mary Altaffer/AP/picture alliance

«የመካከለኛው አፍሪቃ ሪፐብሊክ ለአፍሪቃ ኅብረት የጋራ አቋም ድጋፏን በድጋሚ ይሰጣል።» ሲሉ ፕሬዚዳንት ፎስቲን አርቼንጅ ቱዋዴራ በቅርቡ በተጠናቀቀው በኒው ዮርክ የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ተናግረዋል። ቱዋዴራ "የተባበሩት መንግሥታት ጥልቅ ተሃድሶ እንዲያደርግ እና የጸጥታዉ ምክር ቤት አባላት ፍትሐዊ ተሳትፎ በማድረግ ሁሉም አህጉራት ተወካይ እንዲኖራቸዉ ወንበሮቹን ማስፋት የጠበቅበታል" ሲሉ ነዉ የአፍሪቃ ሕብረትን አቋም የገለፁት።

አፍሪቃ ከጎርጎረሳዉያኑ 2005 ዓ.ም ጀምሮ በተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ ለማግኘት በጥረት ላይ ትገኛለች ሲሉ ለዶቼ ቬለ የተናገሩት የአፍሪቃ አኅጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና የፖሊሲ ኔትዎርክ ኮሙዩኒኬሽን ባለሞያ ኢማኑኤል ቤንሳህ፤ የአፍሪቃ ሕብረት የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤትን ታሳቢ በማድረግ የራሱን የሰላምና የፀጥታ ምክር ቤት ያቋቋመበት አንዱ ምክንያት መሆኑን ገልፀዋል። እንድያም ሆኖ የተባበሩት መንግሥታት በዓለም አቀፍ ደረጃ ብዙ ወገንተኝነት ያለዉ እና ሁሌም እንዲኖረዉ የሚፈልግ ነዉ ሲሉ ነዉ የገለፁት። 

ስለዚህም አሉ የነፃ ንግድ ባለሞያዉ በማከል፤ ስለዚህም የአፍሪቃ ሕብረት በተባበሩት መንግሥታት የጸጥታ ምክር ቋሚ መቀመጫ ለማግኘት ድምፅ ማሰማቱ አስፈላጊ ነው። አፍሪቃ ተጨማሪ ድጋፍ ለማግኘት ከአፍሪቃ ሕብረት ውጭ ተጨማሪ የይሁንታ ድምፆች መጉረፍ አለባቸዉ ሲሉም አክለዋል። የዩክሬይን ጦርነት በአፍሪቃ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ አሳድሯል። የነዳጅና የእህል ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል። ይሁንና ብዙ በአፍሪቃ ብዙ አገሮች በግጭቱ ውስጥ አንድ ወገን ላለመሆን መርጠዋል።

Infografik UN Abstimmung gegen Russland in Afrika EN

የአፍሪቃ ሕብረት ሊቀ መንበር ማኪ ሳል በቅርቡ እንደተናገሩት "ታሪክ እንደሚያሳየዉ አፍሪቃ ብዙ ተሰቃይታለች፤ የአዲስ ቀዝቃዛ ጦርነት ቦታ መሆን አትፈልግም፣ ይልቁንም ለሁሉም አጋሮቿ በጋራ ጥቅም ላይ የዋለ የመረጋጋትና የእድል ምሰሶ መሆን ትፈልጋለች" ሲሉ የአህጉሩ መሪዎች ወገንተኝነት እንዲያሳዩ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የሄደዉን ግፊት በመጥቀስ ተናግረዋል። 

ከዚህ በተጨማሪም ሩሲያና ዩክሬን የሚያካሂዱት ጦርነት ሰፊ የሆነ ዓለም አቀፍ ግጭት እንዳያስከትል  ሁለቱ ሃገራት ወደ ውይይት ጠረጴዛ  እንዲመጡም አሳስበዋል። አዲስ ተመራጩ የኬንያ ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ በመንግሥታቱ ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤው ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ባደረጉት ንግግር፤ የዓለም መሪዎች ከአፍሪቃ ጋር በተያያዘ የወገንተኝነት ጥያቄያቸዉን እንደገና እንዲያጤኑ ጥሪ አቅርበዋል።

«ከዘር ማጥፋት ጭፍጨፋና የእርስ በርስ ግጭት አንስቶ እስከ ግብርናን ማዘመን ብሎም ወረርሽኝን መዋጋት በመሳሰሉት ላይ አፍሪቃ አህጉር የችግሮቹን ዋንኛ መንስኤ ለመቅረፍ ምንም አይነት ድጋፍና ትኩረት አልተሰጠዉም፤ ችላም ተብሏል።  አፍሪቃ አህጉር ለመጨረሻ ጊዜ ጠንካራና ውጤታማ፤ የብዙ ወገንተኝነት ማዕከል የነበረዉ በበርሊኑ ጉባኤ በ 1884 እና 1885 ዓ.ም እንደነበር ታሪክ ያመለክታል። በቀውስ ወቅት ወገንተኝነት ማጣት የአፍሪቃን ህዝብ ከሞራል አሳቢነት ዑደት ውጪ ያደርገዋል፤ ይህ ደግሞ የሰብዓዊነት ዉድቀት ነዉ።»

Libyen I Bunter Markt in Tripolis
ምስል McPhotoStr/Bildagentur-online/picture alliance

የ55 ዓመቱ ፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶ እንዲህ ዓይነቶቹን ቸልተኛነትና የፍትሕ መዛባቶች የሰው ልጆች ውድቀት እንደሆኑ ገልፀዋል። በኬንያ መዲና ናይሮቢ የጫማ ነጋዴ የሆኑት ሲኩ ካማው እንደሚሉት የምዕራቡ ዓለም ለአፍሪቃ የተሻለ ጥቅም አለዉ ብዬ አላምንም። 

«የምዕራቡ ዓለም ለአፍሪቃ የተሻለ ጥቅም አለው ብዬ አላስብም። ለአፍሪቃ የተሻለ ጥቅም ቢኖራቸው ኖሮ፣ አፍሪቃ እነሱ እንደበለፀጉት ትበለፅግ ነበር ብዬ አምናለሁ። አፍሪቃ እንደ አንድ አህጉር አንድ ብትሆን፣ እንደ አህጉር ተባብራ መስራትና ምዕራባውያንን ችላ ማለት ብትችል ኖሮ፣ ከምዕራቡ ዓለም ጋር መስራትና የምዕራቡን ፍላጎት ከማድረግ ጋር ልንወዳደር እንችል ነበር።»

በናይሮቢ ነዋሪ የሆነችዉ ሌላዋ ነጋዴ ክሪስቲና ፔትሮ የሲኩ ካማውን ሃሳብ ትጋራለች። «እንደ ኬንያዊ ወይም በአጠቃላይ አፍሪቃውያን እንደመሆናችን መጠን የምንሰጠው ብዙ ነገር አለን። በአንድ ምክንያት ብቻ እኛ ለዓለም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ነን። ጀርመንም ሆነ ፈረንሳይ ከናይጀሪያ ወይም ከጋና የበለጠ አስፈላጊ አይደሉም። አፍሪቃ በዓለም አቀፍ ደረጃ በአንደኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች። እኛ አንደኛ ደረጃ ላይ በመሆናችን የሌሎች አገሮች ድርሻና የሌሎች አገሮች ሁሉ ሚና በዓለም አቀፍ ደረጃ አንድ መሆን አለበት ብለን መቆም ነዉ። እንደ አፍሪቃውያን አንድ ከሆንን ያንን ሚና ማሳካት እንችላለን። ስለዚህ የአፍሪቃ መሪዎች ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ይልቅ በፓን አፍሪካ ጉዳዮች ላይ በማተኮር ራሳቸውን ማስተዳደር ይኖርባቸዋል። ምክንያቱም እንዲህ ካደረግን አብረን እየጠነከርን እናድጋለን።»

 East African Community Headquarters in Arusha, Tanzania
ምስል Veronica Natalis/DW

እንደ ጎርጎረሳዉያኑ አቆጣጠር በ 2018 የተቋቋመዉ የአፍሪቃ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና (AfCFTA) 43 ፓርቲዎች ና 11 ፈራሚዎች ያካተተ ነዉ። የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ከዓለም የንግድ ድርጅት ቀጥሎ  የዓለማችን ትልቁ የነፃ ንግድ ክልል በመሆኑም ይታወቃል። በናይሮቢ፤ የዩናይትድ ስቴትስ ዓለም አቀፍ ዩኒቨርሲቲ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ መምህር  ኤልያስ ሙኒ ለዶቼ ቬሌ እንደገለጹት አፍሪቃ በዓለም አቀፍ መድረክ ላይ መገኘቷን የገደበውን ቀይ ምንጣፍ ቆርጣ በንግዱ ዓለም አንድ መሆን ትችላለች።

«እንቅፋቶች መኖራቸው ልናደርገው አንችልም የሚል ነገር መሆን የለበትም። የምስራቅ አፍሪቃ ጉዳይ ምን ያህል ከባድ እንደሆነ ጥሩ ምሳሌ ይመስለኛል። ነገር ግን የምስራቅ አፍሪቃ ማህበረሰብ ከነዚህ እንቅፋቶች በአንዳንዶቹ አንፃር ዕድገት ሲያደርግ ቆይቷል። በእኔ አመለካከት በአፍሪቃ በአህጉር ደረጃ ልንወጣው የሚገባን ትልቁ ድክመት ወይም ጉዳይ፣ ለምሳሌ ያህል፣ በከፍተኛ ታክስ ምክንያት ለተከሰተው የአፍሪቃ ውስጥ ንግድ እንቅፋቶች ነው። ይህን ለማሻሻል ጥሩ ምሳሌ ያላቸው አንዳንድ የምስራቅ እስያ ሀገሮች ያደረጉት ማየት ነው።» እንደ ሙኒ አባባል ከሆነ በአፍሪቃ አህጉር ደረጃ ያለው ትልቁ ድክመት በከፍተኛ ትርፍ ምክንያት ለአፍሪቃ ውስጥ ንግድ እንቅፋት ሆንዋል ነው።      

አዜብ ታደሰ / ክሪስፒን ማክዊዴዎ

ታምራት ዲንሳ