1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አጣብቂኝ ዉስጥ የገባዉ የፈረንሳይ ፖለቲካና ፕሬዚዳንቱ

ሐሙስ፣ ሰኔ 16 2014

የፈረንሳይ ፖለቲካ በአሁኑ ወቅት መስቀለኛ መንገድ ላይ መሆኑ በስፋት እየተነገረ ይገኛል። ለዚህም ባለፈዉ ሳምንት መጨረሻ እሁድ የተካሄደዉን የብሔራዊ ምክርቤት እና የሕግ አዉጭ አባላትን ምርጫ ተከትሎ በተገኘዉ ዉጤት ነዉ።

https://p.dw.com/p/4D8zK
Frankreich Emmanuel Macron
ምስል Eliot Blondet/abaca/picture alliance

ማክሮ የገጠማቸዉ የፖለቲካ ኪሳራ

 

የፈረንሳይ ፖለቲካ በአሁኑ ወቅት መስቀለኛ መንገድ ላይ መሆኑ በስፋት እየተነገረ ይገኛል። ለዚህም ባለፈዉ ሳምንት መጨረሻ እሁድ የተካሄደዉን የብሔራዊ ምክርቤት እና የሕግ አዉጭ አባላትን ምርጫ ተከትሎ በተገኘዉ ዉጤት ነዉ። በዉጤቱ ለሁለተኛ የስልጣን ዘመን የተመረጡት የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኤማኑኤል ማክሮ ፓርቲ በምክር ቤት አነስተኛ መቀመጫን አግኝቶአል። ዉጤቶ የፈረንሳይን ፖለቲካ አጣብቂኝ ዉስጥ ከቶታል ተብሎአል። ፕሬዚዳንት ማክሮ ካጋጠማቸዉ ከዚህ የፖለቲካ ኪሳራ ለመዉጣትም ከሌሎች የፈረንሳይ መንግሥት ተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር ጥምረት በመፍጠር የብሔራዊ አንድነት መንግሥት ለማቋቋም ሃሳብ በማቅረብ የየፓርቲዎችን አመራራሮች ጠርተዉ በማነጋገር ላይ ናቸዉ። 


ሃይማኖት ጥሩነህ 


አዜብ ታደሰ 
ነጋሽ መሐመድ