አጠያያቂው የአውሮጳ ህብረት አቅምና ተሰሚነት
ረቡዕ፣ ጥር 6 2012ማስታወቂያ
የኢራንና የዩናይትድ ስቴትስ ግጭት እንዲሁም የሊቢያው ጦርነት እና የውጭ ኃይሎች ጣልቃ ገብነት የአውሮጳ ህብረትን እየተፈተኑ ነው።ህብረቱ ኢራንን ከዓለም አቀፉ ማህብረሰብ ጋር ለማስማማት ብዙ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል። ኢራን ኒዩክልየርን ለሰላማዊ ጥቅም ብቻ እንድታውል የተስማማችበት የኒዩክልየር ውል ላይ እንድትደርስ ብዙ አስተዋጽኦም አድርጎ ነበር ።በሊቢያም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትን ድጋፍ ያገኘው የጠቅላይ ሚኒስትር ፋይዝ አል-ሳራጅን መንግሥት እየደገፈ ነው። ሆኖም ራሳቸውን የብሔራዊ ጦር ጠቅላይ አዛዥ ብለው የሰየሙት የጀነራል ኸሊፋ ሀፍጣር ኃይሎች የሊቢያ መንግሥት መቀመጫ ወደሆነችው ትሪፖሊ ሲገሰግሱ ህብረቱ ተጽእኖ ማድረግ አለመቻሉ እያነጋገረ ነው። የዛሬው አውሮጳ እና ጀርመን ዝግጅታችን በአጠያያቂው የአውሮጳ ህብረት አቅምና ተሰሚነት ላይ ያተኩራል። ገበያው ንጉሤ ያቀርብልናል።
ገበያው ንጉሤ
ኂሩት መለሰ