1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ትምህርትአፍሪቃ

አዳማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን በቅርቡ ሊያስመርቅ ነው

ረቡዕ፣ ኅዳር 23 2013

በቅርቡ የተመራቂ ተማሪዎችን ቅበላ ከፈጸሙ ዩኒቨርሲቲዎች አንዱ የኾነው አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ከጥቂት ሳምንታት በኋላ ተማሪዎችን ለማስመረቅ መዘጋጀቱን ዐስታወቀ። በትግራይ ክልል በተቀሰቀሰው ግጭት ምክንያት ለአንድ ወር ተቋርጦ የነበረው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሪዎች ጥሪም ዳግም ተጀምሯል።

https://p.dw.com/p/3m8FG
12.06.2013 DW Online Karten Basis Äthiopien Englisch

ታኅሣስ 10 ቀን፣ 2013 ዓ.ም. የምረቃ ስነ ስርዓት ይከናወናል ተብሏል

በቅርቡ የተመራቂ ተማሪዎችን ቅበላ ከፈጸሙ ዩኒቨርሲቲዎች አንዱ የኾነው አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ከጥቂት ሳምንታት በኋላ ተማሪዎችን ለማስመረቅ መዘጋጀቱን ዐስታወቀ። በትግራይ ክልል በተቀሰቀሰው ግጭት ምክንያት ለአንድ ወር ተቋርጦ የነበረው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሪዎች ጥሪም ዳግም ተጀምሯል። ግጭቱ ባለፈዉ ጥቅምት 24 ከመከሰቱ አስቀድመው የተመራቂ ተማሪዎችን ቅበላ ከፈጸሙ ዩኒቨርሲቲዎች መካከል አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ አንዱ ነዉ። ዩኒቨርሲቲው ባለፉት አራት ሳምንታት የመማር ማስተማር ሂደቱን ቀጥሎ ታኅሣስ 10 ቀን፣ 2013 ዓ.ም. የምረቃ ስነ ስርዓት አከናውናለሁ ብሏል። የሃሮማያ እና የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ኃላፊዎች በበኩላቸው ነገሮች አሁን ወደ ተረጋጋ ሁኔታ ተመልሰዋል ተብሎ በመታመኑ ለተመራቂ ተማሪዎች ዳግም ጥሪ አድርገናል ብለዋል፡፡ ከትግራይ ክልል እና ከአጎራባች አከባቢዎች የሚመጡ ተማሪዎችን በተመለከተ ግን በተለየ ሁኔታ የሚስተናገዱ ይሆናል ነው የተባለው። የኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲዎች የመማር-ማስተማሩ መርሐ ግብር በጎሳ ግጭትና በኮቪድ 19 ስርጭት ምክንያት ባለፉት ዓመታት ሲደነቃቀፍ ነበር።
ሥዩም ጌቱ 
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ነጋሽ መሐመድ