አዲስ የስደተኞች ውል
ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 2 2011ማስታወቂያ
በጎርጎሪዮሳዊው 2015ዓ.ም በአውሮጳ የተከሰተውን የስደተኞች ቀውስ ተከትሎ የተሰዳጆች ጉዳይ ከፍተኛ ዓለም አቀፍ ተግዳሮት ሆኖ ቆይቷል። የመንግሥታቱ ድርጅት ታዲያ ችግሩ በጋራ ኃላፊነት እና ትብብር ለመፍታት ያስችላል ብሎ ይህን ውል አዘጋጅቶ መንግሥታቱ ላለፉት ሁለት ዓመታት ሲደራደሩበት ነበር። እንዲያም ሆኖ ስደተኞችን በተመለከተ የመንግሥታቱ ድርጅት ጫና ሊያደርግ ነው ከሚል ስጋት የውሉ ምንነት ሃገራትን ሲያሳስብ እንደቆየ ነው የተነገረው። አሁን መንግሥታት የተስማሙበት ውል አስገዳጅ አለመሆኑም ተመልክቷል። ዘጋብያችን ከብራስልስ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።
ገበያው ንጉሤ
ሸዋዬ ለገሠ
እሸቴ በቀለ