1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አዲስ አበባና የነዋሪዎቿ ተቃዉሞ 

ሰኞ፣ መስከረም 7 2011

በአዲስ አበባና  አካባቢዋ ላይ በተከሰተው ሁከት እጃቸው አለበት የተባሉ ከ600 መቶ የሚበልጡ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄኔራል ዘይኑ ጀማል ከጥቂት ሰዓታት በፊት በሰጡት መግለጫ አሳዉቀዋል።

https://p.dw.com/p/352XZ
Äthiopien Proteste in Addis Abeba
ምስል picture-alliance/AP Photo/M. Ayene

አዲስ አበባና የነዋሪዎቿ ተቃዉሞ 


ኮሚሽነሩ በቡራዩ እጃቸው አለበት ተብለው የተያዙ ከ300 አስከ 400 የሚደርሱ ተጠርጣሪዎች ፤  በአዲስ አበባ ደግሞ ከ300 በላይ ተጠርጣሪዎች መያዛቸውን  ነዉ የተናገሩት፡፡ በብጥብጡ  የሰዎች ህይወት መጥፋቱን ንብረት መዉደሙንም ተናግረዋል። ትናንት የታየዉን ግጭት እና ከፍተኛ ችግር ተከትሎ ዛሬ አዲስ አበባ  ላይ በተደረገው የተቃዉሞ ሰልፍ አብዛኛው ህዝብ ሐሳቡን በነፃነት ገልፆ ወደ ቤቱ ተመልሶአል። ነገር ግን  አንዳንድ የተለየ ዓላማ ያላቸው ቡድኖች መረጋጋት እንዳይኖር አንዳንዶቹ ቦምብ ጭምር ይዘው እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል ብለዋል ኮሚሽነሩ፡፡ በመርካቶና በፒያሳ ዝርፊያ ለማካሄድ ሲንቀሳቀሱ ከነበሩት ቡድኖች መካከል ፖሊስ የተወሰኑትን በቁጥጥር ስር አውሏል ብለዋል። የተወሰኑት ከሰላማዊ ሰልፉ ወጣ በማለት ከፖሊስ መሳሪያ ጭምር ለመንጠቅ እንቅስቃሴ አድርገዋል፡፡ በዚህ ምክንያት ሌሎች የጸጥታ ኃይሎች በወሰዱት እርምጃ 5 ግለሰቦች መሞታቸውና የተወሰኑት ደግሞ መቁሰላቸውን ኮሚሽነር ዘይኑ ጀማል ተናግረዋል። የዛሬዉን የአዲስ አበባን የተቃዉሞና የቁጣ ሰልፍ በአራትኪሎ፤ ሽሮ ሜዳ እና  መዘጋጃቤት አካባቢን የቃኘዉ ወኪላችን ዮሐንስ ገብረግዚአብሄር ደግሞ ይህን ዘገባ ከአዲስ አበባ ልኮልናል።

ዮሐንስ ገብረግዚአብሄር

አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሐመድ