አዲስ አበባ በግድያ ማግስት
እሑድ፣ ሰኔ 16 2011ማስታወቂያ
ባሕር ዳርና አዲስ አበባ ዉስጥ በባለስልጣናት ላይ ትናንት የተፈፀመዉ ጥቃትና ግድያ ዛሬ የአብዛኛዉ ኢትዮጵያዊ ትልቅ ርዕሥ ሆኖ ነዉ የዋለዉ።የአዲስ አበባ ነዋሪዎች፣ ፖለቲከኞችና የመንግስት ባለስልጣናትም የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ የተባለዉ ሴራና የባለስልጣናትን ግድያ ሲያወግዙ፣ ምክንያቱን ሲጠይቁ፣ መላምቶችንም እያነሱ ሲጥሉ ነዉ የዋሉት።የኢንተርኔት አገልግሎት ከትናንት ማታ ጀምሮ በመቋረጡ በማሕበራዊ መገናኛ ዘዴዎች የሚሰራጩ ዘገቦችን መከታታል አልተቻለም።
ሰለሞን ሙጬ
ነጋሽ መሐመድ
እሸቴ በቀለ