1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አዲስ አበባ በምርጫው መዳረሺያ

ዓርብ፣ ሰኔ 11 2013

ካለፈው አንድ ወር ግድም አንስቶ እስከትናንት በስትያ ረቡዕ ድረስ ሞቅ ቀዝቀዝ እያለ፤ ረቡዕ ደግሞ እጅግ ተጋግሞ የነበረው የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች የፖለቲካ ክርክር፣ የምረጡኝ ዘመቻ ከትናንት ጀምሮ ቆሟል። ሐሙስ ግን ከተማይቱ ከረቡዕ ተቃራኒ ወደ ቀድሞ የባተሌነት ድባቧ ተመልሳ ነበር።

https://p.dw.com/p/3v9mQ
Äthiopien Wahlkampf in Addis Abeba
ምስል Negash Mohammed/DW

ከረቡዕ ተቃራኒ ወደ ቀድሞ የባተሌነት ድባቧ ተመልሳ ነበር

ካለፈው አንድ ወር ግድም አንስቶ እስትናንት በስትያ ረቡዕ ድረስ ሞቅ ቀዝቀዝ እያለ፤ ረቡዕ ደግሞ እጅግ ተጋግሞ የነበረው የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች የፖለቲካ ክርክር፣ የምረጡኝ ዘመቻ ከትናንት ጀምሮ ቆሟል። በተለይ ርዕሰ ከተማይቱ አዲስ አበባን ካለፈው ረቡዕ ጀምሮ የታዘበው ባልደረባችን ነጋሽ መሀመድ እንደዘገበው የረቡዕ ዕለቱ የጎዳና ላይ የምርጫ ቅስቀሳ ከተማይቱን በአንድ በኩል አጨናንቋት የወትሮ እንቅስቃሴዋንም አስተጓጉለው ነበር የዋሉት። ሐሙስ ግን ከተማይቱ ከረቡዕ ተቃራኒ ወደ ቀድሞ የባተሌነት ድባቧ ተመልሳ ነበር። 

እርግጥ ነው በዘንድሮው ምርጫ ገዢውን ፓርቲ በብርቱ ይፎካከራሉ ተብለው ከሚጠበቁ የፓለቲካ ፓርቲዎች አንዳዶቹ ተገፋን በሚል ምክንያት እራሳቸውን ከምርጫው አግልለውል። የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግርስ ኦፌኮና የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ኦነግ ተደጋግሞ ይጠቀሳሉ።

በብዙ አካባቢዎች በፀጥታ መደፍረስና በዝግጅት ወይም በሎጅስቲክ መጔደል ምክንያት ምርጫ አይደረግም። ከመራጩ ሕዝብም አንዳንዱ የሚፈልገው ፓርቲ ስለማይውዳደር፤ ሌላው ባካባቢው አሁን ምርጫ ስለማይደረግ፣ አብዛኛው ፀጥታ ስጋት ስላልተለየው በኑሮ  ውድነትም አሳቦ ለምርጫው ብዙ ትኩረት እንደማይሰጥው ይናገራል።

ከትናንት በስቲያ ሮብ ጧት አዲስ አበባ ከገባንበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ምሽት ድረስ ያየነው ግን ተቃራኒውን ነው።በመኪና አጀቦች፣መኪናላይ በተጠመዱ ትላልቅ ድምፅ ማጉያዎች የሚደረገው የፖለቲካ ፓርቲዎች የመረጡኝ ዘመቻ፣ ከየደጋፊዎቻችው መፈክር፣ጭፈራና ዘፈን ጋር ተዳምሮ የከተማይቱን አውራ መንገዶች አጨናንቀው፣የወትሮ እንቅስቃሴዋንም አጉለው ነው ነበር የዋሉት።

Äthiopien Wahlkampf in Addis Abeba
ምስል Negash Mohammed/DW

ሐሙስ ግን ከተማይቱ ክምርጫ ትኩሳት ወደ ወትሮዋ ባተሌነት በንጋት ተለውጣለች።ምክንያት የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የጥሞና ጊዜ ያለውን የአራት ቀናት ዝምታ በመደንገጉ ነው።በድንጋጌው መሰረት ጋዜጠኞች ስለምርጫ ዘመቻው አይዘግቡም።ፖለቲከኞችን ወይም እጩዎችን ቃለ መጠይቅ አያደርጉም።እንዲያውም ቦርዱ በፌስ ቡክ ገፁ እንደፃፈው መገናኛ ዘዴዎች የቦርዱን መረጃዎች ማስተጋባት አለባቸው ብሎም ያዛል።

ነፃ ምርጫ ይመራል፣በነፃነት ይሰራል የሚባለው መስሪያ ቤት መገናኛ ዘዴዎች በነፃነት እንዳይዘግቡ ያዛል።ምርጫው የሚደረገው የፀጥታው ስጋት ቢቀንስም ጨርሶ ባልተወገደበት ወቅት ነው።ፖሊስም እንደ ምርጫ ቦርድ ፀጥታ ለማስከበር በሚል ሰበብ የምል-የማደርገውን አስተጋቡ ይል ይሆን።የአዲስ አበባ ፖሊስ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮማንደር ፋሲካ ፋንታ እንደዚያ አይነት ትዕዛዝ የለም ባይ ናቸው።ፀጥታ ማስከበሩ የፖሊስ ፋንታ ነው።ለዚያም ተዘጋጅቷል  ኮማንደር እንዳሉት።
 ድምፅ
የምርጭውን ሂደት ሰላማዊ ለማድረግም የአዲስ አበባ ፖሊስ ፈረቃ እፍርሶ ባንደኛ ደረጃ ተጠንቀቅ 24 ሰአት እየሰራ ነው።እንደገና ኮማንደር ፋሲካ።
 ድምፅ
አዲስ አበባ አብዛኛው ኢትዮጵያም የጥሞና ከተባለለት የ4 ቀን ድብት ላንዳንዱ እፎይታ ሰኞ ሲፈታ እንደገና ምርጫ፣ድምፅ መስጠት መቁጠር ይላል። አሸናፊና ተሸናፊን ይለያልም። ነጋሽ መሀመድ ለዶቸቤለ ከአዲስ አበባ።
ነጋሽ መሀመድ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ሸዋዬ ለገሰ