1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አዲስ ቤተ መጻህፍት በፓሪስ የኢትዮጵያ ኤምባሲ

ሐሙስ፣ ግንቦት 11 2014

ፓሪስ የሚገኘው በፈረንሳይ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በቅርቡ አዲስ ቤተ-መጻህፍት አስመርቋል።ቤተ-መጻህፍቱ የተቋቋመው ከተለያዩ በጎ ፈቃደኞች በተበረከቱ መጻህፍት ነው።

https://p.dw.com/p/4BXys
Frankreich, Paris | Neue Bibliothek in der Botschaft von Äthiopien
ምስል Haimanot Tiruneh/DW

አዲስ ቤተ መጻህፍት በፓሪስ የኢትዮጵያ ኤምባሲ

ፓሪስ የሚገኘው በፈረንሳይ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በቅርቡ አዲስ ቤተ-መጻህፍት አስመርቋል።ቤተ-መጻህፍቱ የተቋቋመው ከተለያዩ በጎ ፈቃደኞች በተበረከቱ መጻህፍት ነው። ቤተ መጻህፍቱ  የተቋቋመበት ዓላማ ፈረንሳይ ለሚገኙ ወጣት ትውልደ ኢትዮጵያውያንና ተመራማሪዎች የኢትዮጵያን ባህል ቋንቋና ታሪክ ጠብቆ መያዝ ነው።መጻህፍቱን ካበረከቱት መካከል ፓሪስ የሚኖሩት የኦሎምፒክ ኮሚቴ አማካሪና የስፖርት ጋዜጠኛ ፍቅሩ ኪዳኔ እንዲሁም ከሁለት ዓመት በፊት በሞት የተለዩት ፕሮፌሰር ከፍሌ ብጽአት ይገኑበታል።

Frankreich, Paris | Neue Bibliothek in der Botschaft von Äthiopien
ምስል Haimanot Tiruneh/DW

ፍቅሩ ኪዳኔና ፕሮፌሰር ክፍሌ በህይወት ዘመናቸው ያጠራቀሟቸውን መጻህፍት ነው በስጦታ ያበረከቱት።  በቤተ መጻህፍት ምረቃ ላይ የተገኘችው የፓሪስዋ ዘጋቢያችን ሃይማኖት ጥሩነህ በዛሬው የባህል መድረክ ስለ ጠቀሜታውና ዓላማው ቀጣዩን ዝግጅት አሰናድታለች።
ሃይማኖት ጥሩነህ 
ኂሩት መለሰ