የስደተኞች ረቂቅ ሕግ
ማክሰኞ፣ ኅዳር 23 2012ማስታወቂያ
ፈረንሳይ የውጭ ዜጎችን ለሥራ በኮታ ወደ ሃገርዋ የማስገባት እቅድ እንዳወጣች መንግሥት በቅርቡ አስታውቋል።ይኽው የኮታ አሠራር በመጪው ዓመት በሃገሪቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ሥራ ላይ ይውሏል ተብሏል። በአዲሱ እቅድ መንግሥት ከአሠሪዎች ጋር የሰለጠነ የሰው ኃይል እጥረት ያሉባቸውን የሥራ መስኮች ለይቶ እንደሚያቀርብ ፤ክፈቱቱን ለመሙላትም ለቦታው አስፈላጊ የሆኑ የውጭ ዜጎችን ቅጥር እንደሚያመቻች አስታውቋል።ሆኖም አሠሪዎች በክፍት የሥራ ቦታቸው የፈረንሳይ ዜጋ መቅጠር ያልቻሉበትን ምክንያት ማስረዳት ይኖርባቸዋል።
የሠለጠነ የውጭ ባለሞያን ወደ ፈረንሳይ የማስገባቱ እቅድ ከቀኝ ጽንፈኞች እና የውጭ ዜጎች ፈረንሳይ መግባታቸውን ከሚቃወሙ ወገኖች ተቃውሞ እየቀረበበት ነው።ዝርዝሩን የፓሪስዋ ዘጋቢያችን ሃያማኖት ጥሩነህ በዛሬው አውሮጳ እና ጀርመን ዝግጅታችን ታቀርብልናለች።
ሃይማኖት ጥሩነህ
ኂሩት መለሰ