1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አዲሱ የኮሮና ዝርያ የደቀነው ስጋት

ማክሰኞ፣ ኅዳር 21 2014

የዓለም ጤና ድርጅት አዲሱና በደቡብ አፍርካ ተገኘ የተባለው የኮሮና  ተሐዋሲ በዓለም የኮቪድ ወረርሺን ዳግም ሊያስፋፋ ይችላል ሲል አስጠንቅቋል። በድርጅቱ ኦሚክሮን የሚል ስያሜ የተሰጠው ይህ ተዋሲ በአንድ ስማንት ጊዜ ውስጥ ከደቡብ አፍርካና ጎረቤቱቿ አልፎ  በአውሮፓህብረት አገሮች፤ በብርታኒያ፤ ክናዳና ጃፓን ጭምር የተዛመተ መሆኑ ታውቁል።

https://p.dw.com/p/43fcT
Neue COVID-19-Variante Omicron
ምስል Pavlo Gonchar/Zumapress/picture alliance

የኮቪድ ወረርሺን ዳግም ሊያስፋፋ ይችላል

አዲስ እና ልውጥ የኮሮና ዝርያ ዓለማችን ላይ ስጋት ደቅኗል። ይህ ኦሚክሮን የሚል ስያሜ የተሰጠው አዲስ ዝርያ ዓለም ላይ መከሰቱን ያገኙት የደቡብ አፍሪቃ ሐኪሞች ቢሆኑም ቀሪው ዓለም ወደ ደቡብ አፍሪቃ የሚያደርገውን ጉዞ ማቋረጡ ተገቡ አይደለም እያለች ነው። የዓለም ጤና ድርጅት ልውጡ ተሐዋሲ በዓለም የኮቪድ ወረርሺን ዳግም ሊያስፋፋ ይችላል ሲል አስጠንቅቋል።ተሐዋሲው በአንድ ስማንት ጊዜ ውስጥ ከደቡብ አፍርካና ጎረቤቶቿ ባሻገር በአውሮፓ ኅብረት አገሮች፤ በብርታኒያ፤ ካናዳና ጃፓን ጭምር የተዛመተ መሆኑ ታውቁል።

የዓለም የጤና ድርጅት ዳይሬተር  ዶክተር ቴድሮስ  አድሀኖም  ከትናንት ጀምሮ ለሦስት ቀናት በጀኔቭ እየተክሄደ ባለው የዓለም የጤና ድርጅት ልዩ ስብሰብ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ ዓለም ለዚህ አዲስ አደገኛ ተሐዋሲና ሊከተል ለሚችለው ወረርሺኝ  በአንድነት ምላሽ እንዲሰጥ ጥሪ አቅርበዋል።

ይህ አዲስ የኮቪድ ዝርያ ያለውን አደገኝነት በሚገባ ልንርዳው ይገባል። የዚህ አዲስ ዝርያ መከስት ግን የኮቪድ ወረርሺን ተወተነዋል ብለን ከሆነ፤ ገና መሆናችንን የሚያስገነዝበን ነው። ዘወትር በስጋት ላይ ነው ያለነው። የተደረጉት ጥረቶችና የተገኙት ውጤቶች በቀላሉ ሊጠፉ ይችላሉ። ስለዚህ አሁን ዋናው ትኩረታችን ይህንን ወረርሺኝ ማጥፋት ላይ መሆን አለበት፤በማለት ለሁሉም መንግስታትና አገሮች  ጥሪያቸውን አስተላለፈዋል።  ዶክተር ቴድሮስ ይህ ተዋህሲ በፍጥነት የመዛመት አቅም ያለው ከመሆኑ ውጭ ገና ብዙ ያልታወቀ መሆኑንም አውስተው፤ ስለተዋህስዊና ስለሚያከትለው ህመም የለው መረጃ ውስንመሆኑን ገልጸዋል ድምጽ  ኦሜክሮን  የበለጠ ተላላፊ፣ ከፍተኛ ህመም የሚያስከትል ፣ ክትባት ሊከላከለው የሚችል ስለመሆን አለምሆኑ ገና በውል አልታወቀም በማለት ሳይንቲስቶች እነዚህን ጥያቄዎች ለመመለስ በርትተው እየሰሩ እንደሆነ አስታውቀዋል። ከዚሁ ጋርም ዶክተር ቴድሮስ  በአጠቃልይ ግን  የኮቪድ ወረርሺን ለመከላከልና ለማጥፋት ክትባትን በሁሉም ቦታ ማዳረስና ለዚህም አለማቅፍ ትብብር መፍጠር ወሳን መሆኑን አጥብቀው አሳስበዋል።

Neue COVID-19-Variante Omicron
ምስል Pavlo Gonchar/Zumapress/picture alliance

የአዲሱን ተዋህሲ በደቡብ አፍርካ  መከሰት ተከትሎ በርካታ አገሮች የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰዱነው፡፤ የአውሮፓ ህብረት አገሮች፣ብርታኒያ፤ ክናዳና ጃፓን ጭምር ከደቡብ አፍርካና ከሌሎች ያካባቢው አገሮች የሚደረጉ በረርዎችን ዓግደዋል። ሌሎች የመከላከያ ደንበሮችንም በስራ ላይ እንዲውሉ አዘዋል።፤ከነዚህ ሁሉ እርምጃዎች ይበልጥ ግን ዜጎች እንዲከተቡና የተክተቡትም ሶስተኛ ክትባት እንዲወስዱ እያበረታቱ ነው። ብርታኒያ ከአስራ ስምንት አመት በላይ ላሉ ዜጎቿ የሶስተኛ የማጠናከሪያ ያ ክትብት የምትሰጥ መሆኑን አስትውቃለች። ከዚህ አንጻር ወረርሺኙ የበለጠ የሚስፋፋውና የከፋ ጉዳትም ሊያደርስ የሚችለው በአብዛኛው ክትባት ባልደረሳቸው የአፍርካ አገሮች ላይ ሊሆን እንደሚችል ነው የሚግመተው።  የአውሮፓ ኮሚሽን ፕሪዝዳንት ኡርሱላ ቮንዴር ላየየን ስለአዲሱ የኮቪድ ዝርያ ሙሉ መረጃ ለማግኘት ቢያንስ ከሁለት እስከ ሶስት ሳምንታት የሚያስፈልጋ መሆኑን በማስገንዘብ ዘጎች ግን  መከተብና የአፍና አፍንጫ ጭንብል መልበስ እንዲሁም ሌሌቹን የመከላከያ ህግጋት ማከብር የሚገባቸው መሆኑን ባለፈው ዕሁድ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስገንዝበዋል።

 ደቡብ አፍርካ የተዋህሲውን ዝርያ ማግኘቷ ብቻ ሳይሆን በወቅቱም በማስታወቋ የተመሰገነች ቢሆንም የጉዞ እገዳ የተደረገባት በመሆኑ ግን ስሞታ እያሰማች ነው። ፕረዝዳንቷ ሚስተር ሲሪል ራማፉዛ  በሰጡት መግለጫ አገራቸው ሀላፊነቷን በተወጣች ዋጋ እየክፈለች ነው በማለት ምእራባውያንን ወቅሰዋል ድምጽ። በተጣለብን  የጉዞ እገዳ በጣም አዝነናል።  እርምጃው ስህተትና ባለፈው የሮሙ የቡድን 20 አገገሮች  ጉባኤ ቃል ከተገባው ያፍነገጠ ነው።ፍጹም ትክክል ያልሆነና ደቡብ አፍርካንና ጎሬቤቶቿን  የሚያገል ነው በማለትም እርምጃው የአገሮቹን ኢኮኖሚ በመጉዳት በሺታውን እዳይከላኩ ከሚያደርጋቸው በስተቀር የተዋህሲውን ስርጭጥ አያገደውም ብለዋል።

ከአውርፓውያኑ የክረመት ወቅት ጋር በተያያዘ የኮቪድ ወረርሺኝ  በብዙ የአውሮፓ አገሮች ዳግም እያገረሸ መሆኑ እየተስተዋለ ሲሆን፤ ከዚህ አዲስ ተዋሲ መፈጠርና መዛመት ጋር ግን ወረርሺኑ የበለጠ እንዳይይሳፋ መንግስታት የበኩላቸውን ሁሉ እያደረጉ ነው_። ሆኖም ግን የኮቪድ ወረርሺ አገሮች በተናጠል በሚወስዱት እርምጃ ብቻ ሊወገድ እንደማይችል መገንዘብና  ያደጉት አገሮች ለብቻቸው በሚወስዷቸው እርምጃዎች ወይንም ለህዝባቸው ሶስተኛ ክትባት ጭምር በመስጠት ከዚህ ተዋህሲና ክሚያስከትለው ወረርሺኝ መዳን እንድማይችሉ ነው ነው የሚታመነው። ከዚህ አንጻር  በጅኔቫ እየተካሄደ ያለው የአለም የጤ ድርጅት ልዩ ጉባኤ የኮቪድንም ሆነ ሌሎች ወረርሺኞችን ለመቋቋም የሚያስችል የትብብር መድረክ ለመፍጠር መሰረት ይጥል ይሆን በማለት ብዙዎች አንጋጠው እንዲያዩ አድርጓቸዋል።

ገበያው ንጉሴ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ነጋሽ መሐመድ