አዲሱ የእስራኤል መንግሥት
ሰኞ፣ ሰኔ 7 2013ማስታወቂያ
በእስራኤል ዛሬ አዲስ መንግሥት ተመስርቷል። የቤንያሚን ነታንያሁ የ12 ዓመታት የጠቅላይ ሚኒስትርነት ሥልጣን ዛሬ አብቅቷል። የተለያየ አቋም የያዙ ፓርቲዎች የተሰባሰቡበት ሰላሳ ስድስተኛው የእስራኤል መንግሥት ዛሬ ሥራውን ጀምሯል። በእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትርነት ዛሬ ቃለ መሃላ የፈጸሙት የ49 ዓመቱ የአይሁድ ብሔረተኞች ፓርቲ መሪ ናፍታሊ ቤኔት ከሀገሪቱ ብሔራዊ የፀጥታ ጉዳዮች አማካሪ ማብራሪያ ተስጥቷቸዋል። ከዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደንም ጋር በስልክ ተወያይተዋል። ዛሬ በተሰየመው የአዲሱ መንግሥት ካቢኔ ውስጥ ትውልደ ኢትዮጵያዊት ሚኒስትር ይገኙበታል። ስለ አዲሱ መንግሥት ምንነት ፈተናዎቹና የህዝቡና የመገናና ብዙሀን አስተያየት የኢየሩሳሌሙን ዘጋቢያችንን አነጋግረናዋል።
ሰሎሞን ሙጬ
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ