1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አዲሱ የአውሮጳ ኅብረትና የብሪታንያ ግንኙነት

ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 27 2013

ከጎርጎሮሳዊው ጥር አንድ 2021 ማለትም ከዛሬ 5 ቀን ወዲህ የሁለቱ ወገኖች ግንኙነት «የንግድና የትብብር ስምምነት»በተባለው አዲስ ውል እየተመራ ነው።ከ2021 መጀመሪያ አንስቶ የብሪታንያ ዜጎች በኅብረቱ አባል ሃገራት ፣የአባል ሃገራት ዜጎችም በብሪታንያ የመኖር እና የመስራት ነጻነታቸው አብቅቷል። በነጻነት የመንቀሳቀስ መብታቸው ተገድቧል።

https://p.dw.com/p/3nXhm
Brüssel | Johnason bei von der Leyen Brexit Gespräche
ምስል Aaron Chown/AFP/Getty Images

ውይይት፦አዲሱ የአውሮጳ ኅብረትና የብሪታንያ ግንኙነት

ብሪታንያ ከአውሮጳ ኅብረት አባልነት እንድትወጣ ብሪታንያውያን በህዝበ ውሳኔ ካጸደቁ ከአራት ዓመት ተኩል በኋላ ብሪግዚት ባለፈው አርብ እውን ሆኗል።የአውሮጳ ኅብረትና ከኅብረቱ በመውጣት የመጀመሪያ የሆነችው ብሪታንያ ከአንድ ዓመት በፊት በስምምነት ከተለያዩ በኋላ፣ ረዥም ጊዜ በወሰደ ድርድር፣ በመጨረሻው ሰዓት ላይ  ከ10 ቀናት በፊት አንድ የጋራ የንግድ ውል ላይ መስማማት ችለዋል። ከጎርጎሮሳዊው ጥር አንድ 2021 ማለትም ከዛሬ 5 ቀን ወዲህ የሁለቱ ወገኖች ግንኙነት «የንግድና የትብብር ስምምነት» በእንግሊዘኛው ምህጻር TCA  በተባለው አዲስ ውል እየተመራ ነው።ከ2021 መጀመሪያ አንስቶ የብሪታንያ ዜጎች በኅብረቱ አባል ሃገራት ፣የአባል ሃገራት ዜጎችም በብሪታንያ የመኖር እና የመስራት ነጻነታቸው አብቅቷል።ምንም እንኳን የአጭር ጊዜ ቆይታ ቪዛ ባያስፈልገውም፣የቀድሞው በነጻነት የመንቀሳቀስ መብታቸው ቀርቷል።የሸቀጦች ዝውውር በብሪታንያና በአውሮፓ ኅብረት ድንበሮች እንዲሁም በብሪታንያም በሰሜን አየርላንድና በብሪታንያ ድንበሮች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር ተግባራዊ ሆኗል። በ2021 አንድ የተባለው  አዲሱ የአውሮጳ ኅብረትና የብሪታንያ ግንኙነት የዛሬው አውሮጳና ጀርመን ዝግጅታችን ትኩረት ነው።በጉዳዩ ላይ እንዲወያዩልን ሦስት አውሮጳ የሚገኙ ወኪሎቻችን ጋብዣለሁ።  እነርሱም ገበያው ንጉሴ ከብራሰልስ፣ድልነሳ ጌታነህ ከለንደን እንዲሁም ሃይማኖት ጥሩነህ ከፓሪስ ናቸው። ከታች የሚገኘውን የድምጽ ማዕቀፍ በመጫን የመጀመሪያውን ክፍል ውይይት ማዳመጥ ትችላላችሁ።

ኂሩት መለሰ

ነጋሽ መሐመድ