1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች ሮሮ

ሰኞ፣ ነሐሴ 20 2011

ተቃዋሚዎች አዋጁ የፖለቲካ ምህዳሩን የማስፋት ዓላማውን የሳተ እና ሀሳባችንንም ያላካተተ ነው ሲሉ ተቃውመዋል። የኢትዮጵያውያን ብሔራዊ ንቅናቄ (ኢብን) እና የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) በሰጡት አስተያየት በአዋጁ ሀገር አቀፍ ፓርቲዎች 10 ሺህ አባላት ማስመዘገብ እንዳለባቸው መደንገጉም አግባብ አይደለም ሲሉ ተችተዋል።

https://p.dw.com/p/3OWAH
Äthiopien Ablehnung Wahlentwurf
ምስል DW/Y. Geberegziabeher

የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሮሮ

የኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባለፈው ቅዳሜ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ ያፀደቀው የኢትዮጵያ  የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የስነ ምግባር አዋጅ በተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች እየተተቸ ነው። ተቃዋሚዎች አዋጁ የፖለቲካ ምህዳሩን የማስፋት ዓላማውን የሳተ እና ሀሳባችንንም ያላካተተ ነው ሲሉ ተቃውመዋል። ለዚሁ ጉዳይ ከተጣመሩ 57 ፓርቲዎች መካከል የኢትዮጵያውያን ብሔራዊ ንቅናቄ (ኢብን) እና የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) በሰጡት አስተያየት በአዋጁ ሀገር አቀፍ ፓርቲዎች 10 ሺህ አባላት ማስመዘገብ እንዳለባቸው መደንገጉም አግባብ አይደለም ሲሉ ተችተዋል። በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤቱ ስብሰባ ላይም "10 ሺህ አባላት ማስፈረም ያልቻለ ፓርቲ ሌላ ሥራ ቢሰራ ይሻላል" መባሉም እንዳስከፋቸው ተናግረዋል። የፓርቲዎቹን አመራሮች ያነጋገረው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ተጨማሪ ዘገባ አለው።
ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር
ኂሩት መለሰ
ተስፋለም ወልደየስ