1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

«ቅንጅት ለዴሞክራሲና ለነጻነት»

ረቡዕ፣ ጥቅምት 5 2012

ድሬደዋን ጨምሮ ከሶማሌ ክልል የተለያዩ ዞኖችና ወረዳዎች የተውጣጡ አባላትና ደጋፊዎች ተገኝተውበታል የተባለው የአዲሱ ፓርቲ መስራች ጉባዔ ላይ የፓርቲው ፕሮግራም ቀርቧል።የፓርቲው መስራች ኮሚቴ የህዝብ ግንኙነትና ቅስቀሳ ኃላፊ አቶ አደን አዲሱ ድርጅት እንዲሰፋ እንፈልጋለን ብለዋል።ማንኛውም ዓላማውን የሚደግፍ ሁሉ የሚሳተፍበት መሆኑንም ገልፀዋል፡፡

https://p.dw.com/p/3RNSD
Die neue Alliance for Democracy and Freedom Partie Konferenz
ምስል DW/Mesay Teklu

በሶማሌ ክልል የተቋቋመው አዱሱ «ቅንጅት ለዴሞክራሲና ለነጻነት» ፓርቲ

«ቅንጅት ለዴሞክራሲና ለነፃነት በሚል ስያሜ የተቋቋመ አዲስ የፖለቲካ ፓርቲ ሰሞኑነን በድሬደዋ መስራች ጉባዔውን አካሂዷል ፡፡ጥምረቱ የሶማሌ ክልል ህዝብንና ብሎም የኢትዮጵያ እዝቦች ዴሞክራሲዊ  መብትና  ነፃነት እንዲከበር እታገላለሁ ብሏል፡፡ ትናንት በድሬደዋ የመስራች ጉባዔውን ያካሄደው የአዲሱ ፓርቲ መስራች ኮሚቴ የህዝብ ግንኙነትና ቅስቀሳ ኃላፊ አቶ አደን አላሊ ለዶቼቬለ DW ፓርቲውን አሁን መመስረት ስላስፈለገበት ምክንያት አስረድተዋል ፡፡ክልሉን እየመራ የሚገኘው ገዢ ፓርቲ በክልሉ ህዝብ በአግባቡ የተወከለ እና አሳታፊ  ነው ብለን አናምንም ብለዋል። ድሬደዋን ጨምሮ ከሶማሌ ክልል የተለያዩ ዞኖችና ወረዳዎች የተውጣጡ አባላትና ደጋፊዎች ተገኝተውበታል የተባለው የአዲሱ ፓርቲ መስራች ጉባዔ ላይ የፓርቲው ፕሮግራም ቀርቧል ፡፡ የፓርቲው መስራች ኮሚቴ የህዝብ ግንኙነትና ቅስቀሳ ኃላፊ አቶ አደን አዲሱ ተቋቋሚ ድርጅት ሰፊ እንዲሆን እንፈልጋለን ብለዋል ፤ ማንኛውም ዓላማውን የሚደግፍ ሁሉ የሚሳተፍበት መሆኑንም ገልፀዋል ፡፡የከልሉን ገዢ ፓርቲ የሶማሌ ዴሞክራቲክ ፓርቲ / ሶዴፓን ጨምሮ ሶስት ያህል የተቃዋሚ ፓርቲዎች እንዳሉበት በሚነገረው የሶማሌ ክለል አዲስ የተቋቋመመው «ቅንጅት ለዴሞክራሲና ለነፃነት»ፓርቲ በመስራች ጉባዔው አመራሮችን መርጧል የፓርቲውን ፕሮግራም እና  ደንብም አፅድቋል፡፡

መሳይ ተክሉ

ኂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሠ