አዲሱ ልውጡ ተዋሲ ያሳደረው ስጋት
ዓርብ፣ ኅዳር 17 2014ማስታወቂያ
አዲስ ልውጥ የኮሮና ተኅዋሲ ደቡብ አፍሪቃ መገኘቱ ከታወቀ በኋላ ሃገራት የተለያዩ ማስጠንቀቂያዎችን እየሰጡና እርምጃዎችንም ለመውሰድ እየተዘጋጁ ነው። በዓለም ዙሪያ አምስት ሚሊዮን ህዝብ የገደለው የኮሮና ተህዋሲ በተከሰተ በሁለት ዓመቱ ከደቡብ አፍሪቃ ተዛመተ የተባለው አዲሱ ልውጥ የኮሮና ተኅዋሲ በዓይነቱ ዴልታ ከተባለው ልውጥ ተኅዋሲ በበለጠ ፍጥነት የሚዛመት ነው ተብሏል። የአውሮጳ ኅብረት ከደቡብ አፍሪቃ ና ወደ ደቡብ አፍሪቃ የሚደረጉ በረራዎች መታገድ አለባቸው ሲል አስታውቋል።ቤልጂየም በተኅዋሲው የተያዘ ሰው በሀገርዋ እንደተገኘ ያሳወቀች የመጀመሪያዋ የአውሮፓ ኅብረት አባል ሃገር ሆናለት።ገበያው ንጉሴ ከብራሰልስ ዘገባ አለው ።