1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

 አደጋ ጣዮቹ (ኦነግ) ሳይሆኑ አይቀርም

ዓርብ፣ መስከረም 2 2012

ቡራዩ ከተማ በሰፈሩ ፖሊሶች መሐል ትናንት ማታ ቦምብ ያፈነዱት ኃይላት የኦሮሞ ነፃ አዉጪ ግንባር (ኦነግ) አባላት ወይም ደጋፊዎች ሳይሆኑ እንደማይቀሩ የኦሮሚያ መስተዳድር አስታወቀ።ፖሊሶች መሐል በተጣለዉ ቦምብ 8 ፖሊሶችና አዲት ሰራተኛቸዉ ቆስለዋል።

https://p.dw.com/p/3PZTG
Äthiopien Beyenu Areda
ምስል DW/S. Muchie

ፖሊስ፤ 22 ተጠርጣሪዎች ተይዘዋል

ቡራዩ ከተማ በሰፈሩ ፖሊሶች መሐል ትናንት ማታ ቦምብ ያፈነዱት ኃይላት የኦሮሞ ነፃ አዉጪ ግንባር (ኦነግ) አባላት ወይም ደጋፊዎች ሳይሆኑ እንደማይቀሩ የኦሮሚያ መስተዳድር አስታወቀ።ፖሊሶች መሐል በተጣለዉ ቦምብ 8 ፖሊሶችና አዲት ሰራተኛቸዉ ቆስለዋል።አደጋዉን ጥለዋል ተብለዉ የተጠረጠሩ 22 ሰዎች መያዛቸዉን የቡራዩ ከተማ የመንግስት የኮሙኒኬሽን ፅሕፈት ቤት ኃላፊ አስታዉቀዋል።አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ የኢትዮጵያ መንግስት መገናኛ ዘዴዎችን ጠቅሶ እንደዘገበዉ ደግሞ የተያዙት ተጠርጣሪዎች አንድም የኦነግ አባላት፣ አለያም ደጋፊዎች መሆናቸዉን የኦሮሚያ መስተዳድር አስታዉቋል።ከአዲስ አበባ ሰሜን-ምዕራብ 25 ኪሎ ሜትር ርቅት ላይ በምትገኘዉ ቡራዩ አምና መስከረም ላይ ተቀስቅሶ በነበረ ግጭት በትንሽ ግምት ከ60 በላይ ሰዎች ተገድለዋል፣ ብዙ ተፈናቅለዋል። የአዲስ አበባዉ ወኪላችን የከተማይቱን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ኃላፊን አነጋግሯል።

ሰለሞን ሙጬ

ነጋሽ መሐመድ

እሸቴ በቀለ