1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አይደር ሆስፒታል ከሁለት ሳምንታት በኋላ ግልጋሎት መቀጠል እንደሚቸገር ኃላፊው ተናገሩ

ሐሙስ፣ መስከረም 20 2014

በመቐለ ከተማ የሚገኘው አይደር ሪፈራል ሆስፒታል ከሁለት ሳምንታት በኋላ የሚሰጠውን አገልግሎት ለመቀጠል እንደሚቸገር አስታወቀ። የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር ክብሮም ገብረስላሴ "የሆነ ነገር ተፈጥሮ መንገድ ተከፍቶ መድሐኒቶቹ እና ግብዓቶቹ መምጣት ካልቻሉ አሁን ባለን ሁኔታ ከዚያ በላይ መቀጠል የምንችል አይመስለኝም" ሲሉ ተናግረዋል። 

https://p.dw.com/p/416GI
Äthiopien Bürgerkrieg Tigray
ምስል AP/picture alliance

የትግራይ የጤና ተቋማት የገቡበት ችግር

በመቐለ ከተማ የሚገኘው አይደር ሪፈራል ሆስፒታል ከሁለት ሳምንታት በኋላ የሚሰጠውን አገልግሎት ለመቀጠል እንደሚቸገር አስታወቀ።  አንዳንድ አገልግሎቶች ለማቋረጥ መገደዳቸውን የተናገሩት የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር ክብሮም ገብረስላሴ "የሆነ ነገር ተፈጥሮ መንገድ ተከፍቶ መድሐኒቶቹ እና ግብዓቶቹ መምጣት ካልቻሉ አሁን ባለን ሁኔታ ከዚያ በላይ መቀጠል የምንችል አይመስለኝም" ሲሉ ተናግረዋል። 

በሆስፒታሉ ባለው የሕክምና ቁሳቁሶች እጥረት ሳቢያ ከአንድ ጊዜ በላይ ሥራ ላይ መዋል የሌለባቸው ግብዓቶች ዳግም እንደሚያገለግሉ የዶይቼ ቬለው ሚሊዮን ኃይለስላሴ ከባለሥልጣናቱ ተረድቷል። በኢትዮጵያ ፌድራል መንግሥት እና በትግራይ ኃይሎች መካከል የተካሔደው ውጊያ ያስከተለው ዳፋ ጊዜያቸው ያለፈባቸው መድሐኒቶችም "በባለሙያዎች ውይይት እና ውሳኔ መሰረት" ጥቅም ላይ እንዲውሉ አስገድዷል። 

ከትግራይ የጤና ተቋማት 80 በመቶው በጦርነት በመውደማቸውን፣ በመዘረፋቸውን እና ባለሙያዎቻቸው ስለሌሉ ሥራ ላይ  አለመሆናቸውን ክልሉን የሚያስተዳድረው መንግሥት አስታውቋል።  

በጉዳዩ ላይ ዶይቼ ቬለ አስተያየት የጠየቃቸው የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ "እኛ ከክልሉ ጋ ምንም እየሰራን አይደለም" የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

ሚሊዮን ኃይለስላሴ
እሸቴ በቀለ
አዜብ ታደሰ