1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አይ ኤም ኤፍ እና አፍሪቃ

ቅዳሜ፣ መስከረም 5 2011

ዓለም አቀፉ የገንዘብ መርህ ድርጅት፣ አይ ኤም ኤፍ ከአፍሪቃ ጋር ያለው ግንኙነት እንደገና ተነቃቅቷል። ብዙዎቹ የአፍሪቃ ሀገራት ሕዝቦች ግን ከዚሁ ድርጅት ጋር መስራት አይፈልጉም።፣

https://p.dw.com/p/34tHz
USA IWF Haupteingang
ምስል picture-alliance/dpa/J. Lo Scalzo

የአፍሪቃ የውጭ እዳ ሸክም

ይሁንና፣ አፍሪቃውያቱ መንግሥታት የተሸከሙት ግዙፍ የውጭ እዳ ብዙዎቹን ክስረት አፋፍ ላይ ስለጣላቸው በወቅቱ ከዚሁ ድርጅት ጋር መስራት እንዳስገደዳቸው የምጣኔ ሀብት ጠበብት ይናገራሉ።

በነዳጅ ዘይት ሀብቷ የምትታወቀዋ አንጎላ ከጥቂት ጊዜ በፊት፣ ባለፈው ነሀሴ ወር መጨረሻ  የገንዘብ መርህ ድርጅት፣ አይ ኤም ኤፍን ድጋፍ ጠይቃለች።  የአንጎላ ፕሬዚደንት ዦዋዎ ሉሬንሶ ከአይ ኤም ኤፍ  ከብድር ጎን በሀገራቸው ለማካሄድ ያቀዱትን የኤኮኖሚ ተሀድሶ ተግባራዊ ማድረግ የሚያስችላቸውንም ድጋፍ እንደሚያገኙ ተስፋ አድርገዋል።  ሞዛምቢክ፣ ጋና እና የዴሞክራቲክ ኮንጎ ሬፓብሊክን ጨምሮ ሌሎች ዘጠኝ አፍሪቃውያት ሀገራት፣  በአሁኑ ጊዜ ከአይ ኤም ኤፍገንዘብ አግኝተዋል። ዓለም አቀፉ የገንዘብ መርህ ድርጅት እስከ ጎርጎሪዮሳዊው 2017 ዓም መጨረሻ ድረስ በአፍሪቃ ያንቀሳቀሰው መርሀ ግብር  በ2014  ዓም ከነበረው በአራት እጥፍ አድጎ ወደ 7,2 ቢልዮን ዩኤስ  ዶላር  ደርሷል።

አይ ኤም ኤፍ  አሁን በአፍሪቃ ተጠናክሮ መንቀሳቀስ የጀመረበት ድርጊት አፍሪቃ የግዙፍ ዕዳ ተሸካሚ የነበረችባቸውን ጎርጎሪዮሳዊዎቹን 1980 እና 1990ኛዎቹ ዓመታት ያስታውሳል። በዚያን ጊዜ  አንዳንድ ሀገራት ክስረት ላይ የሚወድቁበት ስጋት ተደቅኖባቸው ስለነበር አይኤም ኤፍ  ጠንካራ ቅድመ ግዴታ ያረፈበት አስቸኳይ ብድር ሰጠ። በምላሹ አይ ኤም ኤፍ እና  የዓለም ባንክ አፍሪቃውያቱ ሀገራት ጥጥር ኤኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ተሀድሶ እንዲያደርጉ ጠየቀ።

የዋሽንግተን ገላጋይ ሀሳብ በሚል መጠሪያ የሚታወቀው የአይ ኤም ኤፍ የርዳታ ፓኬት ለግብርናው እና ለኢንዱስትሪው ዘርፎች የሚሰጠው ድጎማ፣ የግብር ቅነሳ እንዲቆም ፣ የመንግሥት ተቋማት ወደ ግሉ እጅ እንዲዛወር እና የነፃ ንግድ ፖሊሲን እንዲያራምድ ጠይቆ ነበር።  ይሁንና፣ አይ ኤም ኤፍ በአፍሪቃውያቱ ሀገራት ላይ የጫነው የተሀድሶ ለውጡ ቅድመ ግዴታ የተጠበቀውን የኤኮኖሚ እድገት በማስገኘት ፈንታ፣ የብድር ተቀባይ ሀገራትን ኤኮኖሚያዊ ችግሮች  እንዳባባሱ በጀርመን የሚገኘው የኪል የኤኮኖሚ ተቋም የአፍሪቃ አጥኚ ራይነር ቲለ ለDW አስረድተዋል።.«የአይ ኤም ኤፍ ማስተካከያው መዋቅር በጣም የተሳካ አልነበረም። ባጭሩ ይህን ማለት የሚቻል ይመስለኛል። እርግጥ፣ አብዛኞቹ ሀገራት ያጋጠሟቸውን የክፍያ ችግሮች ላጭር ጊዜ አሸንፈዋል፣ ይሁንና፣ መዋቅራቸውን ምርታቸውን ፣ ከዚያም  የኤኮኖሚ እድገታቸውን  በዘላቂነት ከፍ ማድረግ እንዲያስችል አድርገው ማስተካከል ሳይችሉ ነው የቀሩት። »

Berlin Staatsbesuch Steinmeier und Joao Lourenco Präsident Angola
ምስል DW/Cristiane Teixeira

አሰራር  ይህን በተከተሉት ዓመታት የአይ ኤም ኤፍ የኤኮኖሚ ጠበብት ራሳቸው ድርጅታቸው የሚከተለውን  አሰራር በጥብቅ ነቅፈዋል። ጠበብቱ በጎርጎሪዮሳዊው 2016 ዓም በድርጅቱ መጽሔት ባወጡት ጽሁፍ ፣ አይ ኤም ኤፍ ባለፉት ጊዜያት ለአፍሪቃውያቱ ሀገራት ካቀረበው የማስተካከያ መዋቅር መካከል ቢያንስ ከፊሉ በህበረተሰቡ መካከል እኩልነትን ያላስገኘ እና በሰበቡም የኤኮኖሚውን እድገት እንዳስተጓጎለ አመልክተዋል።  

የኪል ኤኮኖሚ ተቋም ባልደረባ ራይነር ቲለ እንደሚሉት፣ አይ ኤም ኤፍ  በብድር ተቀባዮቹ አፍሪቃውያት ሀገራት አኳያ ባለፉት ዓመታት  እየተከተለው ያለው የአሰራር ለውጥ  ከተሞክሮዎቹ ትምህርት መቅሰሙን አሳይቷል። 

«አይ ኤም ኤፍ  ይህ ችግር መኖሩን በወቅቱ ተረድቶታል። እና ለማህበራዊ ጉዳዮች ተጨማሪ ትኩረት መስጠት ጀምሯል። ስለዚህ  አይ ኤም ኤፍ ከተሞክሮው የሚማር ድርጅት መሆኑ ሊታወቅ ይገባል።»

ዓለም አቀፉ የገንዘብ መርህ ድርጅት ከብድር ተቀባዮቹ ሀገራት ጋር በአሁኑ ጊዜ በሚያደርገው ግንኙነት ላይ መልካም አስተዳደር፣ እንዲሁም፣ ማህበራዊ ጉዳዮች ለተሰኙት ነጥቦች ከቀድሞው በበለጠ ትኩረት ይሰጣል። ከዚህ በተጨማሪም ድርጅቱ ለሚሰጠው ብድር የሚያስቀምጣቸው ቅድመ ግዴታ እንደበፊቱ ጠንካራ እንደማይሆን ምልክት ታይቷል።   

ለዚህ የአሰራር ለውጥ ምክንያት ሊሆን ይችላል የሚባለው የዓለም አቀፉ የገንዘብ መርህ ድርጅት አይ ኤም ኤፍ እና የዓለም ባንክ ብቸኞቹ የአፍሪቃ መንግሥታት አበዳሪዎች አለመሆናቸው ነው።   አንዳንድ ሀገራት አሁን አሁንከመደበኞቹ የካፒታል ገበያዎች ገንዘብ ማግኘት ችለዋል።  በተለይ፣ ይላሉ  በዳካር በሚገኘው የሮዛ ሉግዘምቡርግ ተቋም ዋና ስራ አስኪያጅ ሴኔጋላዊው የምጣኔ ሀብት ጠቢብ ንዶንጎ ሲይላ ከ DW ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ላይ፣ የትልቋ ወራች ቻይና እድገት በአፍሪቃ ያለውን የፋይናንስ ሁኔታ ለዋውጦታል ይላሉ ።   

«የቻይና መምጣት ለአፍሪቃውያት ሀገራት ክፍያቸውን የሚያከናውኑበት ሌላ አዲስ አጋጣሚ ፈጥሮላቸዋል።  ቻይና ለአፍሪቃውያት ሀገራት አልፎ አልፎ ከአይ ኤም ኤፍ ቁራኛ የሚያመልጡበትን እድል ከፍታላቸዋለች። ምክንያቱም፣ ቻይና ብድር በምትሰጥበት ጊዜ አንዳችም ፖለቲካዊም ሆነ ኤኮኖሚያዊ ተሀድሶ ቅድመ ግዴታ አታቀርብም። ቻይና ከአፍሪቃ የምትፈልገው ንግድ፣ የተፈጥሮ ሀብት፣ ገበያዎች እና መሰል ነገሮችን ነው። »

Mosambik Fischkutter in Maputo
ምስል Reuters/G.L. Neuenburg

ይሁንና፣ የቻይና ብድር አሰጣጥ ፖሊሲ የአፍሪቃውያቱን የእዳ ተሸካሚነት ችግር አያቃልልም፣ ችግሩ ያለው የሚከተሉት ፖሊሲ ላይ ነው ባይ ናቸው።
«አፍሪቃውያት ሀገራት በመሰረቱ የዕዳ ተሸካሚ የሚሆኑት በንግዱ እንቅስቃሴ ውስጥ በዋነኝነት ተሳታፊ ባለመሆናቸው ነው። አብዛኛውን ጊዜ ወደ ውጭ የሚልኩት ያላለቀ ምርት ሲሆን፣ ቀሪውን በንግድ ወደ ሀገር ያስገባሉ። »

በ1980 እና 1990ኛዎቹ ዓመታት እንደታየው በወቅቱ አፍሪቃውያኑን መንግሥታት ለገጠማቸው የእዳ ቀውስ ተጠያቂው የነዳጅ ዘይት፣ የካካዎ ወይም አልማዝን የመሳሰሉ ማዕድናት ዋጋ  በዓለም ገበያ መውደቅ እና የውጭ አበዳሪዎች የእዳውን ወለድ ከፍ ያደረጉበት ሁኔታ ነው።
«አፍሪቃውያት ሀገራት ወደ ውጭ ለሚልኳቸው ምርቶቻቸው የሚያገኙት ዋጋ ዝቅተኛ በመሆኑ እና ከውጭ ለሚያገኙት ብድር የሚጠየቁት ወለድ ከፍ እያለ በመሄዱ የብዙ እዳ ተሸካሚ ሆነዋል። ይህ ነው የ1980ዎቹ ዓመታት እና ያለፉት ዓመታትም  አሰራር ይህ ነበር።» 

 አፍሪቃ ይህን ችግር ልትቀንስ የምትችለው የግብርናው እና ኢንዱስትሪ ዘርፎቿን ማነቃቃት ስትችል መሆኑን ሲይላ አስረድተዋል።
«የባለ እዳነቱን ችግር ከመሰረቱ መመልከት ያስፈልጋል ብየ አስባለሁ። ይህም ለምሳሌ አፍሪቃውያት ሀገራት የግብርና ዘርፋቸውን ማዳበር የሚችሉበት ተጨባጭ ሁኔታ ሊፈጠርላቸው ይገባል። ይህም አይ ኤም ኤፍ፣ የዓለም ንግድ ድርጅት እና የአውሮጳ ህብረት ኮሚሽን በኤኮኖሚያዊ ሽርክና ስምምነቶች  የሚያቀርቡላቸውን የነፃ ንግድ አጀንዳን መቀበል አይኖርባቸውም። »
የቻይናውያኑ ብድር  በተፈጥሮ ሀብት ላይ ብቻ በማተኮር የሚሰጠው የቻይና ብድር ለአፍሪቃ ችግር ዘላቂ መፍትሔ አልሆለመሆኑ የአንጎላ ሁ በምሳሌነት ትጠቀሳለች። 
ጠበብት እንደሚገምቱት፣ አንጎላ በነዳጅ ዘይቷ ሀብት ሽያጭ በምታገኘው ገቢ በመተማመን  በወቅቱ ከቻይና የተበደረችው ገንዘብ 25 ቢልዮን ዩኤስ ዶላር ደርሷል። ይሁንና፣ አንጎላ አሁን የአይኤም ኤፍን ርዳታ መጠየቋን፣ የምጣኔ ሀብት ጠበብት አፍሪቃ ወደፊትም በዋሽንግተን ዓለም አቀፍ የገንዘብ መርህ ድርጅት ላይ ጥገኛ መሆኗ እንደማይቀር ጠቋሚ አድርገው ተመልክተውታል።

Angola Ölförderung vor der angolanischen Küste
ምስል Getty Images/AFP/M. Bureau

«የማስተካከያው መዋቅር በጣም የተሳካ አልነበረም። ባጭሩ ይህን ማለት የሚቻል ይመስለኛል። እና አብዛኞቹ ሀገራት ያጋጠሟቸውን የክፍያ ችግሮች ላጭር ጊዜ አሸንፈዋል፣ ይሁንና፣ መዋቅራቸውን ምርታቸውን ፣ ከዚያም  የኤኮኖሚ እድገታቸውን  በዘላቂነት ከፍ ማድረግ እንዲያስችል አድርገው ማስተካከል አልቻሉም። »
«አይ ኤም ኤፍ  ይህ ችግር መኖሩን በወቅቱ ተረድቶታል። እና ለማህበራዊ ጉዳዮች ተጨማሪ ትኩረት መስጠት ጀምሯል። ስለዚህ  አይ ኤም ኤፍ ከተሞክሮው የሚማር ድርጅት መሆኑ ሊታወቅ ይገባል። »

«የቻይና መምጣት ለአፍሪቃውያት ሀገራት ክፍያቸውን የሚያከናውኑበት አዲስ አጋጣሚ ፈጥሮላቸዋል።  ቻይና አፍሪቃውያት ሀገራት አልፎ አልፎ ከአይ ኤም ኤፍ ቁራኛ እንዲያመልጡ እድሉን ትከፍታለች። ምክንያቱም፣ ቻይና አንዳችም ቅድመ ግዴታ አታቀርብም። ቻይና የምትጠይቀው ንግድ፣ የተፈጥሮ ሀብት፣ ገበያዎች እና መሰል ነገሮችን ነው። »

«አፍሪቃውያት ሀገራት በመሰረቱ የዕዳ ተሸካሚ የሚሆኑት በንግዱ እንቅስቃሴ ውስጥ በዋነኝነት ተሳታፊ ባለመሆናቸው ነው። አብዛኛውን ጊዜ ወደ ውጭ የሚልኩት ያላለቀ ምርት ሲሆን፣ ቀሪውን በንግድ ወደ ሀገር ያስገባሉ። 

«አፍሪቃውያት ሀገራት ወደ ውጭ ለሚልኳቸው ምርቶቻቸው የሚያገኙት ዋጋ ዝቅተኛ በመሆኑ እና ከውጭ ለሚያገኙት ብድር የሚጠየቁት ወለድ ከፍ እያለ በመሄዱ የብዙ እዳ ተሸካሚ ሆነዋል። ይህ ነው የ1980ዎቹ ዓመታት እና ያለፉት ዓመታትም  አሰራር ይህ ነበር።  »

 «የባለ እዳነቱን ችግር ከመሰረቱ መመልከት ያስፈልጋል ብየ አስባለሁ። ይህም ለምሳሌ አፍሪቃውያት ሀገራት የግብርና ዘርፋቸውን ማዳበር የሚችሉበት ተጨባጭ ሁኔታ ሊፈጠርላቸው ይገባል። ይህም አይ ኤም ኤፍ፣ የዓለም ንግድ ድርጅት እና የአውሮጳ ህብረት ኮሚሽን በኤኮኖሚያዊ ሽርክና ስምምነቶች  የሚያቀርቡላቸውን የነፃ ንግድ አጀንዳን መቀበል አይኖርባቸውም።»

አርያም ተክሌ/ያን ፊሊፕ ቪልሄልም

ተስፋለም ወልደየስ