1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አዝማሪ ከያንያን

እሑድ፣ ታኅሣሥ 28 2011

በማሲንቆ እያጀበ ፤ ድምጻዊው እሱ ፣ ደራሲው እሱ፣ የሙዚቃ ተጫዋቹ እሱ ፤ ሙሉ ባንድ ይሉታል፤ አዝማሪን።

https://p.dw.com/p/3B5pi
Azimare singer Yisehak Masinko und Selamnesh Zemene
ምስል Privat

መዝናኛ፦ አዝማሪ ከያንያን

በድምጹ እዛው ባየው ግጥሙን ይፈጥራል። ከሌሎች ታዳሚዎችም “ተቀበል” እየተባለ ያቀነቅናል። ያዝ እንግዲህ ይሉታል። ግጥም ያፈልቁለታል፤ የግጥም ቅብብሎሹ ይደራል፤ ጨዋታው ይደምቃል፤ በባህላዊ አዝማሪ ምሽት ቤት። በድሮ ጊዜ የኅብረተሰብ ድምፅ ነበሩ ይባላል አዝማሪዎች፡፡ ነገሥታትና ገዥዎችም ድምጻቸውን ያሰሙበታል፤ በኅብረተሰብና በወቅቱ በነበሩ ገዥዎች መካከልም የነበረውን ፍትጊያና ቅብብሎሽ የሚያሳይ እንደነበር ይናገራሉ፡፡  የአዝማሪ ምሽቱ ከምሽት ሶስት ሰአት እስከ ዘጠኝ ሰአት ድረስ ደመቅ ብሎ ይዘልቃል። በግጥሞቻቸው እያዋዙ በማሲንቆ ምሽቱን ከሚያደምቁት ውስጥ ሰላምነሽ ዘመነ እና በቅጽል ስሙ ይስሀቅ ማሲንቆ የእሁድ መዝናኛ እንግዶቻችን ናቸው። ከድምፅ ዘገባው ያድምጡ

ነጃት ኢብራሒም

ማንተጋፍቶት ስለሺ