1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አካታች የሰላም ድርድር ጥሪ ያቀረበዉ ኦፌኮ

ዓርብ፣ ሰኔ 24 2014

የኦፌኮ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል አቶ ሙላቱ ገመቹ መንግስት ሰሞኑን ከህወሓት ጋር ድርድር ለማድረግ መዘጋጀቱን ይፋ ባደረገበት መግለጫው ስለሌሎች ታጣቂ ቡድኖች ያለው ነገር አለመኖሩ የድርድሩን ሃቀኝነት ከወዲሁ ጥርጣሪ ውስጥ የሚከት ነው ብለውታል፡፡

https://p.dw.com/p/4DXcq
Äthiopien Oromo Federalist Congress
ምስል DW/Y.G. Egziabhare

አካታች የሰላም ድርድር ጥሪ ያቀረበዉ ኦፌኮ

የኢትዮጵያ ገዢ ፓርቲ ብልጽግና ሰሞኑን በሥራ አስፈጻሚ እና በማዕከላዊ ኮሚቴው በኩል ተወያይቶ በሰሜን ኢትዮጵያ መንግስትን ነፍጥ አንስቶ ከሚወጋው ህዝባዊ ወያኔ ኃርነት ትግራይ (ሕወሓት) ጋር ልዩነቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት እንዲያስችል ኮሚቴ አዋቅሮ ዝግጁነቱን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል፡፡

ገዢ ፓርቲው ይህን ውሳኔ ሲያሳውቅ ከህወሓት ውጪ ኦሮሚያ ክልልን ጨምሮ በተለያዩ አከባቢዎች በመሳሪያ መንግስትን እየተገዳደሩ የሚገኙ ኃይላት በዚህ ድርድር ስለመካተት አለመካተታቸው ያለው ነገር የለም፡፡ የኦሮሞ  ነጻነት ግንባር (ኦነግ) እና የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግሬስ (ኦፌኮ) ከዚህ ቀደም በየፊናቸው ባወጡት የአቋም መግለጫዎቻቸው መንግስት ከህወሓት ጋር ለማድረግ የወጠነው የሰላም ድርድር ኦሮሚያ ውስጥ በሰፊው የሚንቀሳቀሰውን የኦሮሞ  ነጻነት ጦር እና ሌሎች ኃይላትን ማካተት እንዳለበት ጠይቀው ነበር፡፡

የኦፌኮ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል አቶ ሙላቱ ገመቹ ለዶይቼ ቬለ እንደተናገሩት፤ መንግስት ሰሞኑን ህገመንግስታዊ መርህን በመከተል ከህወሓት ጋር ድርድር ለማድረግ መዘጋጀቱን ይፋ ባደረገበት መግለጫው ስለሌሎች ታጣቂ ቡድኖች ያለው ነገር አለመኖሩ የድርድሩን ሃቀኝነት ከወዲሁ ጥርጣሪ ውስጥ የሚከት ነው ብለውታል፡፡

ሥዩም ጌቱ 
ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር
አዜብ ታደሰ