አከራካሪው የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት ና ፌደራሊዝም
ዓርብ፣ ታኅሣሥ 16 2013ማስታወቂያ
ኢትዮጵያ የምትመራበት ሕገ መንግሥትና አወቃቀር አሁንም ፖለቲከኞችንና ምሁራንን እያከራከረ ነው። አንዳንድ ፖለቲከኞች የአሁኑ ሕገ መንግሥትና አደረጃጀት በሌላ መተካት የለበትም ይላሉ። እነዚህ ወገኖች ከዚህ ውጭ በአማራጭነት የሚቀርቡትን አወቃቀሮች አሃዳዊ አምባጋነናዊ ጨፍላቂ በማለት ሲኮንኑ ይሰማሉ። ምሁራንን ጨምሮ ሌሎች አስተያየት ሰጭዎች በፊናቸው ኢትዮጵያን ለቅርብ ጊዜው ጦርነትና ግጭት ዳርጓል የሚሉት ሕገ መንግሥትና አወቃቀር በአዲስ መለወጥ አለበት ሲሉ ይከራከራሉ። ኢትዮጵያ አዲስ ሕገ መንግሥት አያስፈልጋትም ባዮች የእነርሱን ሃሳብ በመቃረን አማራጭ መፍትሄ የሚያቀርቡትን ልዩ ልዩ ስሞች እየሰጡ ማጣጣላቸውንም ስህተት ሲሉ ይተቻሉ። ታሪኩ ኃይሉ ከአትላንታ በዚህ ጉዳይ አንድ ዘገባ አጠናቅሯል።
ታሪኩ ኃይሉ
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ