1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አንጋፋዋ ጋዜጠኛ ኢሌኒ መኩሪያ

ረቡዕ፣ ሐምሌ 14 2013

ጋዜጠኛዋ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በ1957 ዓ.ም ሲቋቋምና ሲመረቅ የወቅቱን የጣቢያውን ሥራ አሥኪያጅ አቶ ሳሙኤል ፈረንጅን ንግግር እንዲያደርጉ የጋበዘች እና እንደ መጀመሪያ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ተናጋሪ የምትቆጠር መሆኗን የቀድሞ ባልደረቦቿ ይናገራሉ። ከጋዜጠኝነቱ በተጨማሪም የሬድዮ እና የቴሌቪዥን ማስታወቂያዎችን በመሥራትም አገልግላለች።

https://p.dw.com/p/3xo2h
Äthiopien Addis Abeba | Radio Journalistin | Elleni Mekuria
ምስል privat

ዜና እረፍት

በኢትዮጵያ የጋዜጠኝነት እድገት ታሪክ ቀዳሚ ከነበሩት አንጋፋ ጋዜጠኞች አንዷ እሌኒ መኩሪያ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች። የኢትዮጵያ ቴሌቪዝን በ1957 ዓ,ም ሲመሠረት የመጀመሪያ አንባቢ መሆኗ የሚነገርላት ጋዜጠኛ እሌኒ ለኢትዮጵያ ራዲዮ እንዲሁም ለዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ለረዥም ዓመታት አገልግላለች። ጋዜጠኛ እሌኒ የኢትዮጵያ ሴት የመገናኛ ብዙሃን ማሕበርን ከመሠረቱና ካጠናከሩ አባላትም አንዷ በመሆን ትታወሳለች። ባደረባት ህመም ምክንያት ለረዥም ጊዜያት በሀገር ውስጥ እና በውጭም ህክምና ስትከታተል የቆየችው ታዋቂዋ ጋዜጠኛ ኢሌኒ መኩሪያ በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም መለየቷን ሰምተናል።

ሰሎሞን ሙጬ 

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ