1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ታማኝ በየነን ለመቀበል ዝግጅቱ ተጠናቋል

ማክሰኞ፣ ነሐሴ 22 2010

ከዓመታት ስደት በኋላ በኋላ ዛሬ ወደ ሃገራቸዉ የገቡ አራት አንጋፋ አርቲስቶች ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸዉ። በሌላ በኩል የፊታችን ቅዳሜ ማለዳ አዲስ አበባ ይደርሳል ተብሎ በጉጉት ስለሚጠበቀዉ አርቲስትና አክቲቪስት ታማኝ በየነ አቀባበል ዛሬ አዲስ አበባ ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰቶ ነበር።

https://p.dw.com/p/33uD4
Äthopien: Rückkehr der Künstlerin Alemtsehay Wadajo
ምስል FBC Fana Broadcasting Corporate S.C.

ታማኝ በየነን ለመቀበል ዝግጅታችንን አጠናቀናል

አርቲስቶቹን ቦሌ ዓለም አቀፍ አየረ ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ መለስዓለም እንዲሁም የአዲስ አበባ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ ባዬ አቀባበል እድርገዉላቸዋል። በቀጣይ ለ 27 ዓመታት በዩናይትስ ስቴትስ ስደት ላይ የነበረችዉና ዛሬ ወደ ሃገርዋ የገባችዉ አርቲስት ዓለምፀሐይ ወዳጆ በብሔራዊ ትያትር ደማቅ አቀባበል ሥነ-ስርዓት ተደርጎላታል። ብሔራዊ ትያትር ከተካሄደዉ የአቀባበል ሥነ-ስርዓት በኃላ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በዛሬው እለት ወደ ሀገራቸው የተመለሱትን አርቲስት ዓለምፀሓይ ወዳጆ፤ አርቲስት አበበ በለው እና አርቲስት ተክሌ ደስታን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።  ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የጥበብ ሰው የጎደለውን የሚተች ብቻ ሳይሆን የጎደለውን የሚሞላ ጭምር ነው ሲሉ መናገራቸዉ ተመልክቶአል። ለዓመታት በአዉስትራልያ ስደት ላይ የነበዉ አርቲስት ተስፋዬ ገብረሃናም ዛሬ አዲስ አበባ ከገቡት አርቲስቶች መካከል አንዱ ነዉ። በሌላ በኩል የፊታችን ቅዳሜ ማለዳ አዲስ አበባ ይደርሳል ተብሎ በጉጉት ስለሚጠበቀዉ አርቲስትና አክቲቪስት ታማኝ በየነ አቀባበል ዛሬ አዲስ አበባ ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰቶ ነበር። ወኪላችን ዮሃንስ ገብረግዚአብሔር ዝርዝሩን ተከታትሎአል። 

ዮሃንስ ገብረእግዚአብሔር

አዜብ ታደሰ 
አርያም ተክሌ