የብራስልስ የመጀመሪያው ጥቁር ከንቲባ
ዓርብ፣ ጥቅምት 9 2011ማስታወቂያ
ቤልጅግ የመጀመሪያውን ጥቁር ከንቲባ ለደቡብ ምዕራብ ብራስልስ ጋንሾረን ማዘጋጃ ቤት መርጣለች። በጎርጎሮሳዊው 1975 ዓ.ም በስደት ወደ ቤልጅግ የመጡት ተመራጩ ከንቲባ ፒየር ኮንፓኒ ባለፈው እሁድ በተካሄደው ምርጫ ከአጠቃላይ ድምጽ 28 በመቶ አግኝተዋል።
ቡካቩ በተሰኘ የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ከተማ የተወለዱት ፒየር የዝነኛው እግር ኳስ ተጫዋችና አምበል ቪንሰንት ኮንፓኒ አባት ናቸው። ልጃቸው ቪንሰንት ለማንችስተር ሲቲና ለቤልጂግ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን የሚሰለፍ ወሳኝ ተጨዋች ነው። የሰሞኑ መነጋገሪያ ስለነበረው ስለእኚህ ከንቲባ ምርጫ የብራስልሱ ዘጋቢያችን ዳግማዊ ሲሳይ ተድላ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።
ዳግማዊ ሲሳይ
ተስፋለም ወልደየስ
ሸዋዬ ለገሠ