1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

«አስቸጋሪ ምርጫዎች» ድራማ፥ ክፍል 9

እሑድ፣ ግንቦት 2 2012

ይህ «አስቸጋሪ ምርጫዎች» በሚል ርዕስ የሚቀርብላችሁ የወንጀል ተፋላሚዎቹ ድራማ ዘጠነኛ ክፍል ነው።

https://p.dw.com/p/3bzqH
DW Crime Fighters Serienmotiv „Uneasy choices“

አስቸጋሪ ምርጫዎች

ይህ «አስቸጋሪ ምርጫዎች» በሚል ርዕስ የሚቀርብላችሁ የወንጀል ተፋላሚዎቹ ድራማ ዘጠነኛ ክፍል ነው። በዛሬው ዘጠነኛ ክፍል የማጋሪያ ከተማ በጭንቀት ተውጣ እናገኛታለን። ምንም እንኳን በዝናባማው ወቅት የኮሌራ ወረርሽኝ እንዳይከሰት ብዙ ጥረቶች የተደረጉ ቢሆንም፤ በርካታ ሰዎች በበሽታው ተይዘው ህክምና እየተሰጣቸው ይገኛል። በሽታው የሚዛመትበት ስረ መሠረቱ ላይ ትኩረት ካልተደረገ  በስተቀር ይበልጥ ብዙ ሰዎች ሊያዙ ይችላል። እስካሁን ከፍተኛ ዝናብ የነበረ ቢሆንም፤ ጎርፍ ግን አልተከሰተም። ያም ሆኖ የፍሳሽ ማስወገጃ ቱቦ መፈንዳት እና የውኃ መበከል ማጋጠሙ በቂ የመጠጥ ውኃ እንዳይኖር ምክንያት ሆኗል። ይህ በእንዲህ እንዳለ፦  የሐይማኖት ሞት ሰበብን ለማግኘት ፖሊስ ምርመራውን ቀጥሏል። የዛሬው«መጀመሪያ ያለው ነገር ሁሉ መጨረሻ አለው» የተሰኘው ዘጠነኛ ክፍል የሚጀምረው ከፖሊስ ጣቢያ ነው።

ደራሲ፦ ፒናዶ አዳማ ዋባ
አዘጋጅ፦ ማንተጋፍቶት ስለሺ