1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በሕወሓት መግለጫ ላይ የተሰጡ አስተያየቶች

ረቡዕ፣ ጥቅምት 5 2012

የህዝባዊ ሓርነት ትግራይ ማእከላይ ኮሚቴ ለሰባት ተከታታይ ቀናት ካደረገው ስብሰባ በኋላ ባወጣው መግለጫ   «ሕጋዊነት የጎደለው» ያለው ውሁድ ፓርቲ የመፍጠሩ ሂደት፣ የሀገሪቱን የፖለቲካ ቀውስ ወደ ባሰ ደረጃ  እየገፋ ያለ እና ግንባሩንና ሀገሪቱን ወደ መበተን ሊደርስ የሚችል አደጋ ነውም ብሎታል።

https://p.dw.com/p/3RP26
Emblem der Tigray People's Libration Font (TPLF)

ህወሀት ከኢህአዴግ እህት ድርጅቶች ጋር ካለው የአመላከት እና ተግባር ልዩነት አኳያ የውህደቱ አካል ይሆናል ተብሎ እንደማይጠበቅ አንድ የፖለቲካ ምሁር አመለከቱ።የህዝባዊ ሓርነት ትግራይ ማእከላይ ኮሚቴ ለሰባት ተከታታይ ቀናት ካደረገው ስብሰባ በኋላ ባወጣው መግለጫ   «ሕጋዊነት የጎደለው» ያለው ውሁድ ፓርቲ የመፍጠሩ ሂደት፣ የሀገሪቱን የፖለቲካ ቀውስ ወደ ባሰ ደረጃ  እየገፋ ያለ እና ግንባሩንና ሀገሪቱን ወደ መበተን ሊደርስ የሚችል አደጋ ነውም ብሎታል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በስመ ውሁድ ፓርቲ እየተደረገ ያለው እንቅስቃሴ ውሁድ ፓርቲ የመፍጠር ሳይሆን አዲስ ፓርቲ የማቋቋም ሥራ ነው ሲልም ወቅሷል።
ሚሊዮን ኃይለ ሥላሴ
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ