1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢትዮጵያ በኮሮና ተኅዋሲ ወረርሽኝ ከአፍሪቃ ሁለተኛ ደረጃን ይዛለች

እሑድ፣ ጥቅምት 7 2014

ባለፈው አንድ ሳምንት ብቻ በኮቪድ 19 ምክንያት የ308 ሰዎች ሕይወት አልፏል።ይህም ወረርሽኙ ኢትዮጵያ መግባቱ ከታወቀበት ጊዜ አንስቶ የተመዘገበ ከፍተኛ የሞት ቁጥር ነው። ባለፈው አንድ ሳምንት ብቻ በየቀኑ በበሽታው የሞተው ሰው ቁጥር በአማካኝ 44 መሆኑንም የወረርሽኙን  አሳሳቢነት አጉልቷል።

https://p.dw.com/p/41ko9
Äthiopien l Start der COVID-19-Impfung
ምስል Solomon Muchie/DW

አሳሳቢው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በኢትዮጵያ

 

ኢትዮጵያ መግባቱ ከታወቀ ሁለተኛ ዓመቱ ላይ የሚገኘው የኮሮና ወረርሽኝ ፣አሁን እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር ሰሞኑን አስታውቋል። የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት ባለፈው አንድ ሳምንት ብቻ በኮቪድ 19 ምክንያት የ308 ሰዎች ሕይወት አልፏል። ይህም ወረርሽኙ ኢትዮጵያ መግባቱ ከታወቀበት ጊዜ አንስቶ የተመዘገበ ከፍተኛ የሞት ቁጥር መሆኑ ተገልጿል። ባለፈው አንድ ሳምንት ብቻ በየቀኑ በበሽታው የሞተው ሰው ቁጥር በአማካኝ 44 መሆኑንም የወረርሽኙን  አሳሳቢነት አጉልቷል። እስካሁን በኮሮና ተኅዋሲ መሞታቸው የታወቀው ሰዎች አጠቃላይ ቁጥር ወደ 6ሺህ ተጠግቷል። ሀገሪቱም በኮሮና ተኅዋሲ ወረርሽኝ ከአፍሪቃ ሁለተኛውን ደረጃ ይዛለች። «አሳሳቢው የኮሮና ተኅዋሲ ወረርሽኝ በኢትዮጵያ» የዛሬው እንወያይ የመነጋገሪያ ርዕስ ነው። በዚህ ርዕስ ላይ ዶክተር ሚክያስ ተፈሬ በኢትዮጵያ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የኮቪድ-19 የድንገተኛ አደጋ ማስተባበሪያ ማዕከል ምክትል ሃላፊ ፣ዶክተር ግርማ አባቢ «ሊያና ሄልዝ ኬር» የተባለው የግል የጤና ተቋም ዋና ስራ አስፈጻሚና የኢትዮጵያ የግል የጤና ተቋማት ማኅበር ምክትል ፕሬዝዳንት እንዲሁም ጋዜጠኛ ተሾመ ኃይሉ ተወያይተዋል። ሙሉውን ውይይት ለማዳመጥ ከታች የሚገኘውን የድምጽ ማዕቀፍ ይጫኑ።

ኂሩት መለሰ