1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አሳሳቢው የኑሮ ውድነት

ሰኞ፣ ነሐሴ 17 2013

በልቶ ማደር፣ ልጆችን ማስተማር ለብዙዎች ቀላል አልሆነም። የውጭ ምንዛሪ እጥረት፣ አብዛኛው ሰው የሚገለገልባቸው ሸቀጦች ከውጪ የሚገቡ መሆን፣ የምርት እጥረት ሳይኖር ምርትን መደበቅ እና ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ ማድረግ፣ የኢኮኖሚ አሻጥር፣ የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ተደማምረው የገቢና ወጪ መራራቅን ማባባሳቸው እየተነገረ ነው

https://p.dw.com/p/3zNoJ
Äthiopien Offener Markt in Hawassa
ምስል Shewangizaw Wegayehu/DW

አሳሳቢው የኑሮ ውድነት

የኑሮ ውድነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሻቀበ ነው። በልቶ ማደር፣ ልጆችን ማስተማር ለብዙዎች ቀላል አልሆነም። የውጭ ምንዛሪ እጥረት፣ አብዛኛው ሰው የሚገለገልባቸው ሸቀጦች ከውጪ የሚገቡ መሆን፣ የምርት እጥረት ሳይኖር ምርትን መደበቅ እና ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ ማድረግ፣ የኢኮኖሚ አሻጥር፣ የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ተደማምረው የገቢና ወጪ መራራቅን ማባባሳቸው እየተነገረ ነው።

መንግሥት የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች የሚያቀርቧቸውን አማራጮች መተግበር አለመቻሉ ዘላቂ መፍትሔ እንዳይገኝ ማድረጉም እንዲሁ።

የዋጋ ግሽበት የሚያስከትለው የኑሮ ውድነት በየትም አገር መኖሩን የሚጠቅሱ ባለሙያዎች የኢትዮጵያ ልዩ የሆነው የግሽበት መጠኑ ዕድገት ከፍተኛ መሆንን ነው።

ሰለሞን ሙጬ

ሸዋዬ ለገሰ