1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አሳሳቢው የኑሮ ውድነት

ረቡዕ፣ የካቲት 24 2013

በኢትዮጲያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየጨመረ የሚገኘው የሸቀጦች ዋጋ ፣ የኑሮ ውድነት እንዲባባስ ምክንያት እየሆነ ይገኛል። የዋጋ ጭማሪው በተለይ አብዛኛው የማህበረሰብ ክፍል ሸማች በሆነባቸው የከተሞች አካባቢ የዜጎች እለታዊ ኑሮ እንዲከብድ አድርጎታል ነው የሚባለው።

https://p.dw.com/p/3q9vt
Äthiopien Offener Markt in Hawassa
ምስል Shewangizaw Wegayehu/DW

የኑሮ ዉድነት፣ ሐዋሳ እንደማሳያ

በኢትዮጲያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየጨመረ የሚገኘው የሸቀጦች ዋጋ፣ የኑሮ ውድነት እንዲባባስ ምክንያት እየሆነ ይገኛል። የዋጋ ጭማሪው በተለይ አብዛኛው የማህበረሰብ ክፍል ሸማች በሆነባቸው የከተሞች አካባቢ የዜጎች እለታዊ ኑሮ እንዲከብድ አድርጎታል ነው የሚባለው። በሐዋሳ ከተማ የመገበያያ ስፍራ ለግብይት የወጡ ሸማቾች እና ሻጮች የኑሮ ውድነቱ እንደከበዳቸው ገልጠዋል። የምጣኔ ሐብት ጉዳዮች ምሁራን የችግሩን ምንጭ ከመሠረቱ ለማወቅ  በመረጃ ላይ የተደገፈ ጥናት አስፈላጊነቱ ላይ አጽንዖት ሰጥተዋል። ያም ሆኖ ግን የምርት ፍላጎት እና አቅርቦት አለመጣጣም፣ የሥራ አጥ ዜጎች መበራከት፣ የሕዝብ ቊጥር እድገት መጨመር እና የማምረቻ ግብአቶች የዋጋ ንረት ለኑሮ ውድነት መባባሱ እንደምክንያትነት ይጠቅሳሉ። መንግሥት ችግሮቹን በሦስት መንገዶች መቆጣጠር እንደሚችል ምሁራን ጠቅሰዋል። ሙሉውን ዝግጅት በድምጽ ማዕቀፉ ማድመጥ ይቻላል።

ሸዋንግዛዉ ወጋየሁ 

ማንተጋፍቶት ስለሺ